እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “በዐሥራ ሁለት ተከታታይ ቀኖች ውስጥ በእያንዳንዱ ቀን ከዐሥራ ሁለቱ አለቆች አንዱ መሠዊያው ለሚቀደስበት ክብረ በዓል የሚሆን መባ ያቀርቡ ዘንድ ንገራቸው።”
1 ቆሮንቶስ 14:40 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ሁሉ ነገር በአግባብና በሥነ ሥርዓት ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ሁሉም በአግባብና በሥርዐት ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ሁሉም በአግባብና በሥርዓት ይሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ሁሉን በአገባብና በሥርዐት አድርጉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን። |
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “በዐሥራ ሁለት ተከታታይ ቀኖች ውስጥ በእያንዳንዱ ቀን ከዐሥራ ሁለቱ አለቆች አንዱ መሠዊያው ለሚቀደስበት ክብረ በዓል የሚሆን መባ ያቀርቡ ዘንድ ንገራቸው።”
መሰብሰባችሁ ለፍርድ እንዳይሆን ከመካከላችሁ የራበው ሰው ቢኖር በቤቱ ይብላ። ስለ ቀረው ነገር እኔ እዚያ ስመጣ ተጨማሪ መመሪያ እሰጣችኋለሁ።
በሥጋ ከእናንተ ብርቅም እንኳ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ፤ በመልካም ሥነ ሥርዓት መኖራችሁንና በክርስቶስ ላይ ያላችሁን ጽኑ እምነት በማየትም ደስ ይለኛል።
አንተን በቀርጤስ የተውኩበት ምክንያት ያልተስተካከለውን እንድታስተካክልና ባዘዝኩህም መሠረት የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን በየከተማው እንድትሾም ነው።