ስለዚህ እግዚአብሔር እያንዳንዱ ሰው በቤተ ክርስቲያን የተለያየ አገልግሎት እንዲኖረው አድርጓል፤ በዚህም መሠረት በመጀመሪያ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛ ነቢያትን፥ ሦስተኛ መምህራንን ሾሞአል። ቀጥሎም ተአምራት የሚያደርጉትን፥ ቀጥሎም የመፈወስ ስጦታ ያላቸውን፥ ሰዎችን የመርዳት ስጦታ ያላቸውን፥ አስተዳዳሪዎችንና በተለያዩ ቋንቋዎች የሚናገሩትን ሰዎች መድቦአል።
1 ቆሮንቶስ 12:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁሉም ሐዋርያት ናቸውን? ሁሉም ነቢያት ናቸውን? ሁሉም መምህራን ናቸውን? ሁሉም ተአምራት የሚያደርጉ ናቸውን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁሉ ሐዋርያት ናቸውን? ሁሉስ ነቢያት ናቸውን? ሁሉስ መምህራን ናቸውን? ሁሉስ ታምራት ያደርጋሉን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁሉም ሐዋርያት ናቸውን? ሁሉስ ነቢያት ናቸውን? ሁሉስ አስተማሪዎች ናቸውን? ሁሉስ ተአምራትን ይሠራሉን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውኑ ሁሉ ሐዋርያትን ይሆናሉን? ሁሉስ ነቢያትን ይሆናሉን? ሁሉስ መምህራንን ይሆናሉን? ለሁሉስ ተአምራትን የማድረግ ኀይል ይሰጣልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁሉ ሐዋርያት ናቸውን? ሁሉስ ነቢያት ናቸውን? ሁሉስ አስተማሪዎች ናቸውን? ሁሉስ ተአምራትን ይሠራሉን? |
ስለዚህ እግዚአብሔር እያንዳንዱ ሰው በቤተ ክርስቲያን የተለያየ አገልግሎት እንዲኖረው አድርጓል፤ በዚህም መሠረት በመጀመሪያ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛ ነቢያትን፥ ሦስተኛ መምህራንን ሾሞአል። ቀጥሎም ተአምራት የሚያደርጉትን፥ ቀጥሎም የመፈወስ ስጦታ ያላቸውን፥ ሰዎችን የመርዳት ስጦታ ያላቸውን፥ አስተዳዳሪዎችንና በተለያዩ ቋንቋዎች የሚናገሩትን ሰዎች መድቦአል።
ሁሉም የመፈወስ ስጦታ አላቸውን? ሁሉም በተለያዩ ቋንቋዎች የመናገር ችሎታ አላቸውን? ሁሉም በተለያዩ ቋንቋዎች የተነገረውን የመተርጐም ችሎታ አላቸውን?