1 ዜና መዋዕል 9:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከብንያም ነገድ በኢየሩሳሌም ለመኖር የሄዱት የሚከተሉት ናቸው፦ የሃሰኑአ ልጅ ሆዳውያ፥ የሆዳውያ ልጅ መሹላም፥ የመሹላም ልጅ ሳሉ፥ የይሮሐም ልጅ ዩብነያ፥ የሚክሪ የልጅ ልጅ የዑዚ ልጅ ኤላ፥ የዩብኒያ ልጅ ረዑኤል፥ የረዑኤል ልጅ ሸፋጥያ፥ የሸፋጥያ ልጅ መሹላም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከብንያማውያን፦ የሐስኑአ ልጅ፣ የሆዳይዋ ልጅ፣ የሜሱላም ልጅ ሰሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከብንያምም ልጆች የሐስኑአ ልጅ የሆዳይዋ ልጅ የሜሱላም ልጅ ሰሉ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከብንያምም ልጆች የሐስኑአ ልጅ የሆዳይዋ ልጅ የሜሱላም ልጅ ሰሎ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከብንያምም ልጆች የሐስኑአ ልጅ የሆዳይዋ ልጅ የሜሱላም ልጅ ሰሉ፤ |
የብንያም ነገድ አባላት፦ ሳሉ፥ የመሹላም ልጅ፥ የዮዔድ ልጅ፥ የፐዳያ ልጅ፥ የቆላያን ልጅ፥ የማዕሤያን ልጅ፥ የኢቲኤልን ልጅ፥ የሻዕያን ልጅ፥
የሕግ ምሁሩ ዕዝራ ለዚሁ ተግባር አመች ይሆን ዘንድ ከዕንጨት በተሠራ መድረክ ላይ ቆሞ ነበር፤ ከእርሱም ጋር በስተቀኙ በኩል የቆሙት ሰዎች ማቲትያ፥ ሼማዕ፥ ዓናያ፥ ኡሪያ፥ ሒልቂያና መዕሤያ ሲሆኑ፥ በስተ ግራው በኩል ደግሞ ፐዳያ፥ ሚሻኤል፥ ማልኪያ፥ ሐሹም፥ ሐሽባዳናህ፥ ዘካርያስና መሹላም ቆመው ነበር።