1 ዜና መዋዕል 8:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኤሁድ ዘሮች ናዕማን፥ አሒያና ጌራ ተብለው የሚጠሩት ናቸው፤ እነርሱም በጌባዕ ይኖሩ ለነበሩት በኋላ ግን ከዚያ ተባረው ወደ ማናሐት ሄደው በዚያ ለኖሩ ቤተሰቦች አለቆች ነበሩ፤ ወደዚያም የመራቸው የዑዛና የአሒሑድ አባት ጌራ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጌባዕ ይኖሩ የነበሩትና በኋላም በምርኮ ወደ መናሐት የተወሰዱት የኤሁድ ዘሮች እነዚህ ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህ የኤሁድ ልጆች ናቸው፤ እነዚህ በጌባ የሚቀመጡ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ናቸው፤ እነርሱም ወደ መናሐትም ተማረኩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚህ የኤሁድ ልጆች ናቸው፤ እነዚህ በጌባ የሚቀመጡ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ናቸው፤ ወደ መነሐትም ተማረኩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህም የኤሁድ ልጆች ናቸው፤ እነዚህ በጌባ የሚቀመጡ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ናቸው፤ ወደ መናሐትም ተማረኩ፤ |
የሔጽሮን የበኲር ልጅ ይራሕመኤል አምስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም የመጀመሪያው ራም ቀጥሎም ቡና፥ ኦሬን፥ ኦጼምና አሒያ ተብለው የሚጠሩ ነበሩ፤
በብንያም ግዛትም ጌባዕ፥ ዓሌሜትና ዐናቶት ተብለው የሚጠሩት ከተሞች ከነግጦሽ ቦታዎቻቸው ለአሮን ልጆች የተሰጡ ነበሩ፤ እንግዲህ ለአሮን ዘሮች ቤተሰብ ሁሉ መኖሪያ የሚሆኑ በአጠቃላይ ዐሥራ ሦስት ከተሞች ነበሩ።
ይዲዕኤል፥ ቢልሃን ተብሎ የሚጠራ ወንድ ልጅ ወለደ፤ ቢልሃም ያዑሽ፥ ብንያም፥ ኤሁድ፥ ከናዕና፥ ዜታን፥ ታርሺሽና አሒሻሐር ተብለው የሚጠሩ ሰባት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤