1 ዜና መዋዕል 7:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤፍሬም ሹቴላሕን ወለደ፤ ሹቴላሕም ቤሬድን ወለደ፤ ቤሬድ ታሐትን ወለደ፤ ታሐት ኤልዓዳን ወለደ፤ ኤልዓዳ ታሐትን ወለደ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኤፍሬም ዘሮች፤ ሱቱላ፣ ልጁ ባሬድ፣ ልጁ ታሐት፣ ልጁ ኤልዓዳ፣ ልጁ ታሐት፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኤፍሬም ልጆች፤ ሹቱላ፥ ልጁ ባሬድ፥ ልጁ ታሐት፥ ልጁ ኤልዓዳ፥ ልጁ ታሐት፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኤፍሬም ልጆች፤ ሱቱላ፥ ልጁ ባሬድ፥ ልጁ ታሐት፥ ልጁ ኤልዓዳ፥ ልጁ ታክት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኤፍሬም ልጆች፤ ሹቱላ፥ ልጁ ባሬድ፥ ልጁ ታሐት፥ ልጁ ኤልዓዳ፥ ልጁ ታሐት፥ |
ታሐት ዛባድን ወለደ፤ ዛባድ ሹቴላሕን ወለደ፤ ኤፍሬም ከሹቴላሕ ሌላ ዔዜርና ኤልዓድ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም የጋት ነዋሪዎችን የቀንድ ከብቶች ሲሰርቁ ተይዘው ተገደሉ፤