1 ዜና መዋዕል 7:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የገለዓድ እኅት ሃሞሌኬት ሦስት ወንዶች ልጆችን ወለደች፤ እነርሱም ኢሾድ፥ አቢዔዜርና ማሕላ ተብለው የሚጠሩት ናቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኅቱ መለኬት ኢሱድን፣ አቢዔዝርንና ማሕላን ወለደች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኅቱ መለኬት ኢሱድን፥ አቢዔዝርን፥ መሕላን ወለደች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኅቱ መለኪት ኢሱድን፥ አቢዔዜርን፥ መሕላን ወለደች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኅቱ መለኬት ኢሱድን፥ አቢዔዝርን፥ መሕላን ወለደች። |
ከዮርዳኖስ በስተ ምዕራብ ያለው ምድር ለቀሩት ለምናሴ ልጆች በየወገናቸው ተሰጠ፤ እነርሱም አቢዔዜር፥ ሔሌቅ፥ አሥሪኤል፥ ሼኬም፥ ሔፌርና ሸሚዳዕ የተባሉት ናቸው፤ የዮሴፍ ልጅ የምናሴ ዘሮች በየወገናቸው የሚከተሉት ናቸው።
ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ “ዖፍራ” ተብላ ወደምትጠራው መንደር መጥቶ ከአቢዔዜር ጐሣ የተወለደው የኢዮአስ ንብረት በሆነው የወርካ ዛፍ ሥር ተቀመጠ፤ የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን ምድያማውያን እንዳያዩት ተሸሽጎ በወይን መጭመቂያው ስፍራ የስንዴ ነዶ ይወቃ ነበር።
ጌዴዎንም በዚያ መሠዊያ ሠርቶ “እግዚአብሔር የሰላም አምላክ ነው” ብሎ ሰየመው፤ (ይህም መሠዊያ እስከ ዛሬ የአቢዔዜር ጐሣ ይዞታ በሆነችው በዖፍራ ቆሞ ይገኛል።)
እርሱ ግን እንዲህ አላቸው፤ “እኔ ካደረግሁት እናንተ ያደረጋችኹት አይበልጥምን? የእኔ ጐሣ በሙሉ ከሠራው ሥራ የኤፍሬም ሰዎች የሠራችሁት ጥቂቱ ሥራ ይበልጣል። የኤፍሬም ወይን ቃርሚያ ከአቢዔዜር ወይን መከር አይሻልምን?