1 ዜና መዋዕል 6:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አልዓዛር ፊንሐስን ወለደ፤ ፊንሐስ አቢሹዓን ወለደ፤ አቢሹዓ ቡቂን ወለደ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አልዓዛር ፊንሐስን ወለደ፤ ፊንሐስ አቢሱን ወለደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አልዓዛር ፊንሐስን ወለደ፤ ፊንሐስ አቢሱን ወለደ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አልዓዛር ፊንሐስን ወለደ፤ ፊንሐስም አቢሱን ወለደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አልዓዛር ፊንሐስን ወለደ፤ ፊንሐስ አቢሱን ወለደ፤ |
ዓምራምም አሮንና ሙሴ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችና ማርያም ተብላ የምትጠራ አንዲት ሴት ልጅ ወለደ። አሮንም ናዳብ፥ አቢሁ፥ አልዓዛርና ኢታማር ተብለው የሚጠሩ ወንዶች ልጆች ነበሩት።
የእግዚአብሔር ታላቅ ኀይል ከእኛ ጋር ስለ ነበረ እነርሱ በቂ ችሎታ ያለውን፥ የማሕሊ ጐሣ የሆነውን ሼሬብያ ተብሎ የሚጠራውን ሌዋዊ ላኩልን፤ እርሱም ዐሥራ ስምንቱን ወንዶች ልጆቹንና ወንድሞቹን አስከትሎ ወደ እኛ መጣ።
ከፊንሐስ ጐሣ ጌርሾም፥ ከኢታማር ጐሣ ዳንኤል፥ ከዳዊት ጐሣ የሸካንያ ልጅ ሐጡሽ፥ ከፓርዖሽ ጐሣ ዘካርያስ ሲሆን፥ ከእርሱ ቤተሰብ ወገን የሆኑ አንድ መቶ ኀምሳ ወንዶች ተመዝግበዋል፤ ከፓሐትሞአብ ጐሣ የዘራሕያ ልጅ ኤልየሆዔናይ ከሁለት መቶ ወንዶች ጋር፥ ከዛቱ ጐሣ የያሐዚኤል ልጅ ሸካንያ ከሦስት መቶ ወንዶች ጋር፥ ከዓዲን ጐሣ የዮናታን ልጅ ዔቤድ ከኀምሳ ወንዶች ጋር፥ ከዔላም ጐሣ የዐታልያ ልጅ የሻዕያ ከሰባ ወንዶች ጋር፥ ከሸፋጥያ ጐሣ የሚካኤል ልጅ ዘባድያ ከሰማንያ ወንዶች ጋር፥ ከኢዮአብ ጐሣ የየሒኤል ልጅ አብድዩ ከሁለት መቶ ዐሥራ ስምንት ወንዶች ጋር፥ ከባኒ ጐሣ የዮሲፍያ ልጅ ሸሎሚት ከአንድ መቶ ሥልሳ ወንዶች ጋር፥ ከቤባይ ጐሣ የቤባይ ልጅ ዘካርያስ ከኻያ ስምንት ወንዶች ጋር፥ ከዓዝጋድ ጐሣ የሃቃጣን ልጅ ዮሐናን ከአንድ መቶ ዐሥር ወንዶች ጋር፥ ከአዶኒቃም ጐሣ ኤሊፌሌጥ፥ ይዒኤልና ሸማዕያ ከስድሳ ወንዶች ጋር፥ እነርሱም ዘግየት ብለው ተመልሰዋል፤ ከቢግዋይ ጐሣ ዑታይና ዛኩር ከሰባ ወንዶች ጋር።
ሙሴም ከየነገዱ አንዳንድ ሺህ ሰው በካህኑ በአልዓዛር ልጅ በፊንሐስ መሪነት ወደ ጦርነት ላካቸው፤ ፊንሐስም ከመቅደሱ አንዳንድ ንዋየ ቅድሳትንና ለጦርነት መቀስቀሻ (ክተት) የሚሆን መለከት በእጁ ይዞ ነበር።
ይህም ከመሆኑ በፊት የእስራኤል ሕዝብ የካህኑን የአልዓዛርን ልጅ ፊንሐስን በገለዓድ ምድር ወደሚገኙት ወደ ሮቤል፥ ወደ ጋድና በምሥራቅ ወደሚኖሩት የምናሴ ነገዶች ሕዝብ ላኩት፤
የአሮን ልጅ አልዓዛርም ሞተ፤ በጊብዓም ተቀበረ፤ እርስዋም በኮረብታማው በኤፍሬም አገር የምትገኝና ለልጁ ለፊንሐስ መኖሪያ የተሰጠች ትንሽ ከተማ ናት።
በዚያን ዘመን የአሮን ልጅ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ በእግዚአብሔር ፊት ያገለግል ስለ ነበረ እግዚአብሔርን ጠየቀ፦ “ወንድሞቻችንን ብንያማውያንን ለመውጋት እንደገና እንውጣን ወይስ እንቅር” ብሎ ጠየቀ። እግዚአብሔርም፥ “ነገ በእነርሱ ላይ ድልን እንድትቀዳጁ አደርጋለሁና ሂዱና ውጉአቸው!” አለ።