ከትውልድ እስከ ትውልድ የነበሩት የዮኤል ዘሮች ሸማዕያ፥ ጎግ፥ ሺምዒ፥ ሚካ፥ ረአያ፥ በዓልና፥ በኤራ ናቸው፤ የአሦራውያን ንጉሠ ነገሥት ቲግላት ፐሌሴር የጐሣ መሪ የነበረውን በኤራን ይዞ በምርኮኛነት ወሰደው።
1 ዜና መዋዕል 5:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዩኤል ጐሣ የሼማዕ የልጅ ልጅ የዓዛዝ ልጅ የሆነው ቤላዕ ናቸው፤ ይህም ጐሣ ይኖር የነበረው በዓሮዔርና ከዚያም በስተሰሜን እስከ ነቦና እስከ ባዓልመዖን ባለው ግዛት ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኢዩኤል ልጅ፣ የሽማዕ ልጅ፣ የዖዛዝ ልጅ ቤላ። እነዚህ ከአሮዔር እስከ ናባውና እስከ በኣልሜዎን ድረስ በሚገኘው ምድር ላይ ሰፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስከ ናባውና እስከ በኣልሜዎን ድረስ በአሮዔር የተቀመጠው የኢዮኤል ልጅ የሽማዕ ልጅ የዖዛዝ ልጅ ቤላ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስከ ናባውና እስከ በኣልሜዎን ድረስ በአሮዔር የተቀመጠው የኢዩኤል ልጅ የሰማዕ ልጅ የዖዛዝ ልጅ ቤላ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስከ ናባውና እስከ በኣልሜዎን ድረስ በአሮዔር የተቀመጠው የኢዮኤል ልጅ የሽማዕ ልጅ የዖዛዝ ልጅ ቤላ፤ |
ከትውልድ እስከ ትውልድ የነበሩት የዮኤል ዘሮች ሸማዕያ፥ ጎግ፥ ሺምዒ፥ ሚካ፥ ረአያ፥ በዓልና፥ በኤራ ናቸው፤ የአሦራውያን ንጉሠ ነገሥት ቲግላት ፐሌሴር የጐሣ መሪ የነበረውን በኤራን ይዞ በምርኮኛነት ወሰደው።
የጺቦን ሕዝብም በቤተ ጣዖታቸው ለማልቀስ ወደ ኰረብታ ይወጣሉ፤ የሞአብ ሕዝብ ስለ ነቦና ስለ ሜዳባ ከተሞቻቸው በከባድ ሐዘን ያለቅሳሉ፤ ከሐዘናቸውም የተነሣ ጠጒራቸውንና ጢማቸውን ተላጭተዋል።
ቤትየሺሞት፥ ባዓልመዖንና ቂርያታይም የተባሉት ዝነኞቹ ከተሞች ሳይቀሩ የሞአብ ጠረፍ የሚጠበቅባቸው ከተሞችን ሁሉ በጠላት እንዲመቱ አደርጋለሁ።
“በሞአብ ምድር በኢያሪኮ ከተማ ፊት ለፊት ወደሚገኙት የዐባሪም ተራራዎች ሂድ፤ ወደ ነቦ ተራራም ውጣ፤ ከዚያም ለእስራኤል ሕዝብ የማወርሳትን የከነዓንን ምድር አሻግረህ ተመልከት፤
ሙሴም ከሞአብ ሜዳዎች ተነሥቶ ወደ ነቦ ተራራ ወጣ፤ ከኢያሪኮም በስተምሥራቅ ወዳለው ወደ ፒስጋ ተራራ ጫፍ ደረሰ፤ ከዚያም እግዚአብሔር ምድሪቱን በሙሉ አሻግሮ እንዲመለከት አደረገው፤ ይኸውም ከገለዓድ ግዛት አንሥቶ በስተ ሰሜን በኩል እስካለው እስከ ዳን ከተማ፥
በሐሴቦን ሆኖ የሚገዛው የአሞራውያን ንጉሥ ሲሖን ነበር፤ ግዛቱም የገለዓድን እኩሌታ በማጠቃለል፥ በአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ከምትገኘው ከዓሮዔር ተነሥቶ በዚያ ሸለቆ መካከል ያለችውን የዐሞናውያን ወሰን እስከሆነው እስከ ያቦቅ ወንዝ ይደርስ ነበር፤