1 ዜና መዋዕል 5:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህም ሁሉ በባሳንና በገለዓድ ግዛቶች፥ በዚያም በሚገኙ ታናናሽ ከተሞች እንዲሁም በሳሮን ምድር የግጦሽ ቦታ ባለበት ስፍራ ሁሉ ይኖሩ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጋዳውያንም በገለዓድ፣ በባሳንና እስከ ዳርቻዋ በሚገኙት መንደሮች እንዲሁም በሳሮን በሚገኙ የግጦሽ ስፍራዎች ሁሉና ከዚያም ወዲያ ዐልፈው ተቀመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በገለዓድም ምድር በባሳን በመንደሮቹም በሳሮንም መሰማሪያዎች ሁሉ እስከ ዳርቻቸው ድረስ ተቀምጠው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በገለዓድም ምድር በባሳን በመንደሮቹም በሳሮንም መሰማርያዎች ሁሉ እስከ ዳርቻቸው ድረስ ተቀምጠው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በገለዓድም ምድር በባሳን በመንደሮቹም በሳሮንም መሰማርያዎች ሁሉ እስከ ዳርቻቸው ድረስ ተቀምጠው ነበር። |
ምድረ በዳዎች በፈኩ አበቦች ይሞላሉ፤ የደስታ መዝሙርም ይዘምራሉ፤ እንደ ሊባኖስ ተራራ ግርማ ያላቸው ይሆናሉ፤ እንደ ቀርሜሎስም ተራራ ወይም እንደ ሻሮን ሸለቆ ክብርን የተጐናጸፉ ይሆናሉ። ሁሉም የእግዚአብሔርን ክብር የአምላካችንንም ግርማ ያያሉ።