1 ዜና መዋዕል 5:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በንጉሥ ሳኦል ዘመነ መንግሥት የሮቤል ነገድ በሀጋራውያን ላይ አደጋ ጥሎ ሁሉንም በጦርነት ፈጃቸው፤ በገለዓድም ምሥራቃዊ ክፍል ያለውን ርስታቸውን ይዞ የራሱ አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሳኦልም ዘመነ መንግሥት በእጃቸው ተመትተው ድል ከተደረጉት አጋራውያን ጋራ ተዋጉ፤ በመላው የገለዓድ ምሥራቃዊ ክፍል የሚገኙትን መኖሪያዎቻቸውን ያዙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሳኦልም ዘመን ከአጋራውያን ጋር ተዋጉ፥ እነርሱም በእጃቸው ተመትተው ወደቁ፤ በገለዓድ ምሥራቅ በኩል ባለው አገር ሁሉ በድንኳኖቻቸው ተቀመጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሳኦልም ዘመን ከስደተኞች ጋር ተዋጉ፥ እነርሱም በእጃቸው ተመትተው ወደቁ፤ በገለዓድ ምሥራቅ በኩል ባለው ሀገር ሁሉ በድንኳኖቻቸው ተቀመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሳኦልም ዘመን ከአጋራውያን ጋር ተዋጉ፥ እነርሱም በእጃቸው ተመትተው ወደቁ፤ በገለዓድ ምሥራቅ በኩል ባለው አገር ሁሉ በድንኳኖቻቸው ተቀመጡ። |