1 ዜና መዋዕል 4:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሽሑርም ናዕራ ከተባለችው ሚስቱ አሑዛም፥ ሔፌር፥ ቴምኒና አሓሽታሪ ተብለው የሚጠሩ ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነዕራም አሑዛምን፣ ኦፌርን፣ ቴምኒን፣ አሐሽታሪን ወለደችለት፤ የነዕራ ዘሮች እነዚህ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነዕራም አሑዛምን፥ ኦፌርን፥ ቴምኒን፥ አሐሽታሪን ወለደችለት። እነዚህ የነዕራ ልጆች ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነዓራም አሑዛምን፥ ኦፌርን፥ ቴማንንና አስትራን ወለደችለት። እነዚህ የነዓራ ልጆች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነዕራም አሑዛምን፥ ኦፌርን፥ ቴምኒን፥ አሐሽታሪን ወለደችለት። እነዚህ የነዕራ ልጆች ናቸው። |