1 ዜና መዋዕል 4:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤሽቶንም ቤትራፋ፥ ፋሴሐና ተሒና ተብለው የሚጠሩትን ሦስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ተሒናም ናሐሽ ተብላ የምትጠራውን ከተማ ቈረቈረ፤ የእነዚህም ዘሮች ሬካ ተብላ በምትጠራ አገር ይኖሩ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤሽቶን ቤትራፋንና ፋሴሐን፣ የዒርናሐሽን ከተሞች የቈረቈረውን ተሒናን ወለደ። እነዚህ የሬካ ሰዎች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤሽቶንም ቤትራ-ፋንና ፋሴሐን የዒርናሐሽንም አባት ተሒናን ወለደ፤ እነዚህ የሬካ ሰዎች ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤስቶንም ቤቶራፋንና ፋሲሓን፥ የቄኔዛዊው የኤሴሎምን ወንድም የነዓስ ከተማ አባት ታሒናን ወለደ፤ እነዚህ የራፋ ሰዎች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤሽቶንም ቤትራፋንና ፋሴሐን የዒርናሐሽንም አባት ተሒናን ወለደ፤ እነዚህ የሬካ ሰዎች ናቸው። |
ቀናዝም ዖትኒኤልና ሠራያ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ዖትኒኤልም ሐታትና መዖኖታይ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤