ከዚያም በኋላ ከሶርያውያን ሰፈር በመነሣት ወደ ሰማርያ ተመልሰው ሄዱ፤ እዚያም እንደ ደረሱ የከተማይቱን ቅጽር በር ዘበኞች ጠርተው “ወደ ሶርያውያን ሰፈር ሄደን ነበር፤ ነገር ግን ምንም ያየነው ሰው ወይም የሰማነው ድምፅ እንኳ የለም፤ ፈረሶችና አህዮች እንደ ታሰሩ ናቸው፤ ድንኳኖቹም ሶርያውያን ትተዋቸው ስለ ሄዱ ባዶአቸውን ናቸው” ሲሉ ነገሩአቸው።
1 ዜና መዋዕል 26:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቤተ መቅደስ ዘብ ጠባቂዎች በየቤተሰቡ በቡድን ተከፍለው ነበር፤ እነርሱም ልክ እንደ ሌሎቹ ሌዋውያን በቤተ መቅደሱ ውስጥ አገልግሎት ነበራቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቤተ መቅደሱም ጠባቂዎች በአለቆቻቸው ሥር ተመድበው ልክ እንደ ቤተ ዘመዶቻቸው ሁሉ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሥራ ለማከናወን ምድብ ተራ ነበራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ወንድሞቻቸው ሆነው በጌታ ቤት እንዲያገለግሉ በየአለቆቻቸው የደጁ ጠባቂዎች ሰሞነኞች እነዚህ ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ወንድሞቻቸው ሆነው በእግዚአብሔር ቤት ያገለግሉ ዘንድ የበረኞች አለቆች በየሰሞናቸው የሚጠብቁ እነዚህ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ወንድሞቻቸው ሆነው በእግዚአብሔር ቤት ያገልግሉ ዘንድ የበረኞች የአለቆች ሰሞነኞች እነዚህ ነበሩ። |
ከዚያም በኋላ ከሶርያውያን ሰፈር በመነሣት ወደ ሰማርያ ተመልሰው ሄዱ፤ እዚያም እንደ ደረሱ የከተማይቱን ቅጽር በር ዘበኞች ጠርተው “ወደ ሶርያውያን ሰፈር ሄደን ነበር፤ ነገር ግን ምንም ያየነው ሰው ወይም የሰማነው ድምፅ እንኳ የለም፤ ፈረሶችና አህዮች እንደ ታሰሩ ናቸው፤ ድንኳኖቹም ሶርያውያን ትተዋቸው ስለ ሄዱ ባዶአቸውን ናቸው” ሲሉ ነገሩአቸው።
ሒልቂያ፥ ጠባልያና ዘካርያስ ተብለው የሚጠሩት ናቸው፤ ከሖሳ ቤተሰብ የቤተ መቅደስ ዘብ ጠባቂዎች የሆኑ በድምሩ ዐሥራ ሦስት አባላት ነበሩ።
የቤተ መቅደሱ የምሥራቃዊ በር ዘብ ጠባቂዎች አለቃ ለነበረው ለሌዋዊው ዩምና ልጅ ለቆሬ ደግሞ፥ ለእግዚአብሔር የሚቀርበውን የበጎ ፈቃድ ስጦታዎች ሁሉ የመቀበልና የማከፋፈል ኀላፊነት ተሰጠው።
ከዚህ በታች ስማቸው የተመለከተው የሌዋዊው የአሳፍ ጐሣ የሆኑ መዘምራንም ንጉሥ ዳዊት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት፥ በተመደበላቸው ስፍራ ነበሩ፤ እነርሱም አሳፍ፥ ሄማንና የንጉሡ ነቢይ ይዱታን ናቸው፤ ሌሎች ሌዋውያን የፋሲካውን መሥዋዕት ያዘጋጁላቸው ስለ ነበር፥ የቤተ መቅደሱ ዘብ ጠባቂዎች ስፍራቸውን አይተዉም ነበር፤