አራት ሺህ የሚሆኑ ደግሞ ለዘብ ጥበቃ ተመደቡ፤ ሌሎች አራት ሺህ ደግሞ ንጉሡ በሚሰጣቸው የሙዚቃ መሣሪያ እግዚአብሔርን በዝማሬ ለማመስገን ተመደቡ።
1 ዜና መዋዕል 26:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቤተ መቅደሱ ዘብ ጠባቂዎች የሆኑ ሌዋውያን የሥራ ምድብ እንደሚከተለው ነው፦ ከቆሬ ጐሣ ከአሳፍ ቤተሰብ የቆሬ ልጅ መሼሌምያ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቤተ መቅደሱ በር ጠባቂዎች አመዳደብ፤ ከቆሬያውያን ወገን፤ ከአሳፍ ወንዶች ልጆች አንዱ የሆነው የቆሬ ወንድ ልጅ ሜሱላም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የደጁም ጠባቂዎች ምድባቸው እንደዚህ ነበር፤ ከቆሬያውያን ከአሳፍ ልጆች የቆሬ ልጅ ሜሱላም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በረኞችም እንደዚህ ተመደቡ፤ ከቆሬያውያን ከአሳፍ ልጆች የቆሬ ልጅ ሜሱላም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በረኞችም እንደዚህ ተመደቡ፤ ከቆሬያውያን ከአሳፍ ልጆች የቆሬ ልጅ ሜሱላም። |
አራት ሺህ የሚሆኑ ደግሞ ለዘብ ጥበቃ ተመደቡ፤ ሌሎች አራት ሺህ ደግሞ ንጉሡ በሚሰጣቸው የሙዚቃ መሣሪያ እግዚአብሔርን በዝማሬ ለማመስገን ተመደቡ።
በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩት ሌዋውያን የሚከተሉት ናቸው፦ የሐሹብ ልጅ ሸማዕያ፤ የእርሱም የቀድሞ አባቶች ከመራሪ ጐሣዎች የነበሩት ዓዝሪቃምና ሐሻብያ ናቸው። ባቅባቃር፥ ሔሬሽና ጋላል፤ የሚካ ልጅ ማታንያ፤ የእርሱም የቀድሞ አባቶች ዚክሪና አሳፍ ናቸው። የሸማዕያ ልጅ አብድዩ የእርሱም የቀድሞ አባቶች ጋላልና ይዱታን ናቸው። የነጦፋ ከተማ ይዞታ በነበረው ግዛት ይኖር በነበረው የኤልቃና የልጅ ልጅ የአሳ ልጅ ቤሬክያ።
አባቱ ዳዊት የደነገጋቸውን መመሪያዎች በመከተልም የካህናቱንና ካህናቱን በሥራና መዝሙር በመዘመር የሚረዱትን ሌዋውያን የየዕለቱን የሥራ መደብ አቀናበረ፤ እንዲሁም የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት ባዘዘው መሠረት የቤተ መቅደሱ ዘበኞች በእያንዳንዱ ቅጽር በር የዕለት ሥራቸውን እንዲያከናውኑ አከፋፍሎ መደበ።
አምላክ ሆይ! በጥንት ዘመን ያደረግኸውን ሁሉ በጆሮአችን ሰማን፤ የቀድሞ አባቶቻችንም በዘመናቸው ስላደረግሃቸው ድንቅ ነገሮች ሁሉ ነግረውናል።
እነርሱ በቤተ መቅደሱ በር ጠባቂነት፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ሰዎች የሚያቀርቡአቸውን መሥዋዕቶች በማረድ፥ እንዲሁም ሰዎችን በማገልገል እንዲሠሩ ይፈቅድላቸዋል።