የይሁዳ ልጆች፦ ዔር፥ ኦናን፥ ሴላ፥ ፋሬስና ዛራሕ ናቸው፤ ዔርና ኦናን ግን በከነዓን ምድር ሞተዋል። የፋሬስ ልጆች ሔጽሮንና ሐሙል ናቸው።
1 ዜና መዋዕል 2:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፋሬስም ሔጽሮንና ሐሙል የተባሉ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የፋሬስ ወንዶች ልጆች፤ ኤስሮም፣ ሐሙል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የፋሬስ ልጆች፤ ኤስሮምና ሐሙል ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የፋሬስ ልጆች፤ ኤስሮም፥ ያሙሔል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የፋሬስ ልጆች፤ ኤስሮም፥ ሐሙል። |
የይሁዳ ልጆች፦ ዔር፥ ኦናን፥ ሴላ፥ ፋሬስና ዛራሕ ናቸው፤ ዔርና ኦናን ግን በከነዓን ምድር ሞተዋል። የፋሬስ ልጆች ሔጽሮንና ሐሙል ናቸው።
ነአሶን የዓሚናዳብ ልጅ፥ ዓሚናዳብ የራም ልጅ፥ ራም የአርኒ ልጅ፥ አርኒ የሔጽሮን ልጅ፥ ሔጽሮን የፋሬስ ልጅ፥ ፋሬስ የይሁዳ ልጅ፥ ይሁዳ የያዕቆብ ልጅ፥
ከፋሬስ አንሥቶ እስከ ዳዊት ያለው የትውልድ ሐረግ የሚከተለው ነው፤ ፋሬስ ሔጽሮንን ወለደ፤ ሔጽሮን አራምን ወለደ፤ አራም ዐሚናዳብን ወለደ፤ ዐሚናዳብ ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶን ሰልሞንን ወለደ፤ ሰልሞን ቦዔዝን ወለደ፤ ቦዔዝ ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድ እሴይን ወለደ፤ እሴይም ዳዊትን ወለደ።