1 ዜና መዋዕል 2:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አፋይምም ዩሺዒ የተባለውን ወንድ ልጅ ወለደ፤ ዩሺዒም ሼሻን የተባለውን ወንድ ልጅ ወለደ። ሼሻንም አሕላይ የተባለውን ወንድ ልጅ ወለደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአፋይም ወንድ ልጅ፤ ይሽዒ፣ ይሽዒም ሶሳን ወለደ። ሶሳን አሕላይን ወለደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአፋይምም ልጅ ይሽዒ፥ የይሽዒም ልጅ ሶሳን፥ የሶሳንም ልጅ አሕላይ ነበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአፋይምም ልጅ ይሲ፥ የይሲም ልጅ ሶሳን፥ የሶሳንም ልጅ አሕላይ ነበረ። የአሕላይም ልጅ ይዳይ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአፋይምም ልጅ ይሽዒ፥ የይሽዒም ልጅ ሶሳን፥ የሶሳንም ልጅ አሕላይ ነበረ። |
ሺሞንም አምኖን፥ ሪና፥ ቤንሐናንና ቲሎን ተብለው የሚጠሩ ወንዶች ልጆችን ወለደ። ዩሽዒም ዞሔትና ቤንዞሔት ተብለው የሚጠሩትን ወንዶች ልጆች ወለደ።
ከስምዖን ዘሮች አምስት መቶ የሚሆኑት ወደ ኤዶም ተራራ ሄዱ፤ እነርሱም ይመሩ የነበሩት በዩሽዒ ልጆች በፐላጥያ፥ በነዓርያ፥ በረፋያና በዑዚኤል ነበር፤