1 ዜና መዋዕል 2:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሔጽሮን ልጅ ካሌብ ዐዙባ የተባለች ሴት አግብቶ ይሪዖት ተብላ የምትጠራ ሴት ልጅ ወለደ፤ ይሪዖትም ዬሼር፥ ሾባብና አርዶን ተብለው የሚጠሩ ሦስት ወንዶች ልጆችን ወለደች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኤስሮም ልጅ ካሌብ ከሚስቱ ከዓዙባና እንዲሁም ከይሪዖት ወንዶች ልጆች ወለደ፤ ከዓዙባ የተወለዱት ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ያሳር፣ ሶባብ፣ አርዶን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኤስሮምም ልጅ ካሌብ ከሚስቱ ከዓዙባ ከይሪዖትም ልጆች ወለደ፤ ልጆቹዋም ያሳር፥ ሶባብ፥ አርዶን ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኤስሮምም ልጅ ካሌብ ዐዙባ የምትባል ሚስት አገባ፥ ይሪዖትንም አገባ፤ ልጆችዋም ያሳር፥ ሶባብ፥ ኤርኖን ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኤስሮምም ልጅ ካሌብ ከሚስቱ ከዓዙባ ከይሪዖትም ልጆች ወለደ፤ ልጆቹዋም ያሳር፥ ሶባብ፥ አርዶን ነበሩ። |
የይራሕመኤል ወንድም የነበረው የካሌብ በኲር ልጅ ስሙ ሜሻዕ ይባል ነበር፤ ይህም ሜሻዕ ዚፍ ተብሎ የሚጠራውን ወንድ ልጅ ወለደ፤ ዚፍም ማሬሻን ወለደ፤ ማሬሻም ኬብሮንን ወለደ፤
ካሌብ ዔፋ ተብላ የምትጠራ ቊባት ነበረችው፤ ከእርስዋም ሐራን፥ ሞጻና ጋዜዝ ተብለው የሚጠሩ ሌሎች ሦስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ሐራንም ጋዜዝ ተብሎ የሚጠራ ሌላም ወንድ ልጅ ወለደ።