በሄድክበት ስፍራ ሁሉ ከአንተ ጋር ነበርኩ፤ ጠላቶችህን ሁሉ ድል አደረግኹልህ፤ በዓለም ላይ እንዳሉት እንደታላላቅ ዝነኞች ሰዎች ስምህን ዝነኛ አደርገዋለሁ።
1 ዜና መዋዕል 17:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሕዝቤ ለእስራኤል ቦታ እሰጣቸዋለሁ፤ እዚያም በገዛ ምድራቸው በሰላም እንዲኖሩ አደርጋቸዋለሁ፤ ግፈኞች እንደ ቀድሞው በፍጹም አያስጨንቁአቸውም፤ ከዚህ በፊት በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሳፍንትን እንደ ሾምኩበት ጊዜ ያለ ችግር ዳግመኛ አይደርስባቸውም፤ ጠላቶችህን ሁሉ አስገዛልሃለሁ፤ እኔ እግዚአብሔርም ንጉሣዊ ቤትህን እንደምሠራልህ እገልጥልሃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የራሳቸውም መኖሪያ ስፍራ እንዲኖራቸው፣ ከእንግዲህ በኋላም እንዳይናወጡ ለሕዝቤ ለእስራኤል መኖሪያ ስፍራ እሰጣቸዋለሁ። ከዚህ ቀደም እንዳደረጉት ክፉዎች ከእንግዲህ አይጨቍኗቸውም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሕዝቤም ለእስራኤል ስፍራን እሰጠዋለሁ፥ በዚያም እተክለዋለሁ፥ በስፍራውም ይቀመጣል፥ ከዚያም በኋላ አይናወጥም፤ ከእንግዲህም ወዲያ እንደ ቀድሞው ዘመን ዓመፀኞች አያስጨንቁትም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሕዝቤም ለእስራኤል ስፍራ አደርግለታለሁ፥ በዚያም እተክለዋለሁ፥ በስፍራውም ይቀመጣል፤ ከዚያም በኋላ አይናወጥም፤ የኀጢአትም ልጆች እንደ ቀድሞው አያስጨንቁትም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሕዝቤም ለእስራኤል ስፍራ አደርግለታለሁ፤ እተክለውማለሁ፤ በስፍራውም ይቀመጣል፤ ከዚያም በኋላ አይናወጥም፤ እንደ ቀድሞው ዘመንና በሕዝቤም በእስራኤል ላይ ፈራጆች እንዳስነሣሁበት ጊዜ ግፈኞች ተመልሰው አያስጨንቁትም፤ ጠላቶችህንም ሁሉ አዋርዳቸዋለሁ። እግዚአብሔር ደግሞ ቤት እንዲሠራልህ እነግርሃለሁ። |
በሄድክበት ስፍራ ሁሉ ከአንተ ጋር ነበርኩ፤ ጠላቶችህን ሁሉ ድል አደረግኹልህ፤ በዓለም ላይ እንዳሉት እንደታላላቅ ዝነኞች ሰዎች ስምህን ዝነኛ አደርገዋለሁ።
በቀድሞ ዘመን እጆችህ ያደረጉትን ድርጊት ሁሉ አባቶቻችን ነግረውናል፤ ይኸውም፥ እነርሱን ለመትከል ሕዝቦችን አባረሃል፤ እነርሱን ለማደላደል ነዋሪዎቹን አጥፍተሃል።
ከብዙ ዓመቶች በኋላ የግብጽ ንጉሥ ሞተ፤ እስራኤላውያን ግን አሁንም በባርነት ቀንበር ሥር በመጨነቅ ርዳታ ለማግኘት በመጮኽ ላይ ነበሩ፤ ጩኸታቸውም ወደ እግዚአብሔር ደረሰ።
ከእንግዲህ ወዲህ በምድርሽ የዐመፅ ድምፅ በድንበሮችሽም ጥፋት ወይም ውድመት አይሰማም፤ ነገር ግን ቅጥሮችሽን መዳን የቅጥር በሮችሽን ምስጋና ብለሽ ትጠሪአቸዋለሽ።
በጽዮን ለሚያለቅሱት ሰዎች በዐመድ ፈንታ የአበባ ጒንጒንን፥ በእንባቸው ምትክ የወይራ ዘይትን በኀዘን ፈንታ የደስታ ዘይትን፥ በዛለ መንፈሳቸው ፈንታ የምስጋና መጐናጸፊያን ለማስገኘት ላከኝ። እነርሱም ክብሩን እንዲገልጡ እግዚአብሔር የተከላቸው “የጽድቅ ዋርካዎች” ተብለው ይጠራሉ።
ከሕዝቦችና ከሀገሮች ሰብስቤ በማውጣት ወደ ሀገራቸው አመጣቸዋለሁ፤ በመኖሪያ ቦታዎችና ውሃ በሚወርድበት ቦታ ሁሉ በእስራኤል ተራራዎች ላይ እመግባቸዋለሁ።
ለአገልጋዬ ለያዕቆብ በሰጠሁትና የቀድሞ አባቶቻቸውም በኖሩባት ምድር ይኖራሉ፤ በዚያችም ምድር እነርሱና ልጆቻቸው ዘሮቻቸውም ሳይቀሩ ለዘለዓለም ይኖራሉ፤ እንደ አገልጋዬ እንደ ዳዊት ያለ ንጉሥ በእነርሱ ላይ ለዘለዓለም ይነግሣል።
ሕዝቤን እስራኤልን በሰጠኋቸው ምድር ላይ እተክላቸዋለሁ፤ ዳግመኛም ከዚያ ተነቅለው አይወጡም፤” ይህን የሚናገር እግዚአብሔር አምላካችሁ ነው።