ዳዊትም እንዲህ ሲል መለሰላት፦ “እኔ ያሸበሸብኩት የሕዝቡ የእስራኤል መሪ ያደርገኝ ዘንድ በአባትሽና በቤተሰቡ ፈንታ ለመረጠኝ እግዚአብሔር ክብር ነው፤ አሁንም ቢሆን እርሱን ለማክበር ከመጨፈር አልገታም፤
1 ዜና መዋዕል 17:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስለዚህ እኔ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ለአገልጋዬ ለዳዊት የምለውን እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘ከበግ እረኝነት አንሥቼ የሕዝቤ የእስራኤል መሪ አደረግኹህ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አሁንም ባሪያዬ ዳዊትን እንዲህ በለው፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ገዥ እንድትሆን ከሜዳ አነሣሁህ፤ ከበግ ጥበቃም ወሰድሁህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም ባርያዬን ዳዊትን እንዲህ በለው፦ ‘የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ አለቃ እንድትሆን አንተን ከማሰማርያው፥ ከበግ እረኝነት ወሰድሁህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም አገልጋዬን ዳዊትን እንዲህ በለው፦ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አንተ መንጋውን ስትከተል በሕዝቤ በእስራኤል ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ ከበግ ጥበቃ መርጬ ወሰድሁህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም ባሪያዬን ዳዊትን እንዲህ በለው ‘የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል “አንተ መንጋውን ስትከተል በሕዝቤ በእስራኤል ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ ከበግ ጥበቃ ወሰድሁህ። |
ዳዊትም እንዲህ ሲል መለሰላት፦ “እኔ ያሸበሸብኩት የሕዝቡ የእስራኤል መሪ ያደርገኝ ዘንድ በአባትሽና በቤተሰቡ ፈንታ ለመረጠኝ እግዚአብሔር ክብር ነው፤ አሁንም ቢሆን እርሱን ለማክበር ከመጨፈር አልገታም፤
“ስለዚህም ለአገልጋዬ ለዳዊት የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ንገረው፤ ‘እኔ አንተን የበግ መንጋ ከምትጠብቅበት መስክ አንሥቼ የሕዝቤ የእስራኤል መሪ አደረግኹህ፤
ከእስራኤል ሕዝብ ጋር በተጓዝኩበት ዘመን ሁሉ እኔ ከሾምኳቸው መሪዎች መካከል አንዱን እንኳ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ቤተ መቅደስ እንዲሠራልኝ የጠየቅሁት አለን?’
በሄድክበት ስፍራ ሁሉ ከአንተ ጋር ነበርኩ፤ ጠላቶችህን ሁሉ ድል አደረግኹልህ፤ በዓለም ላይ እንዳሉት እንደታላላቅ ዝነኞች ሰዎች ስምህን ዝነኛ አደርገዋለሁ።
‘በይሁዳ ክፍለ ሀገር የምትገኚ አንቺ ቤተልሔም ሆይ! ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መሪ ከአንቺ ስለሚወጣ፥ ከይሁዳ ታላላቅ ከተሞች በምንም አታንሺም።’ ”
እንዲሁም የስምዖን ጓደኞች የሆኑት የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ዮሐንስም ተገርመው ነበር። ኢየሱስ ስምዖንን፦ “አይዞህ አትፍራ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሰዎችን የምታጠምድ ትሆናለህ፤” አለው።