1 ዜና መዋዕል 15:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከኬብሮን ጐሣ፥ ኤሊኤል ሰማኒያ ለሚሆኑ የጐሣ አባሎች ተጠሪ ሆኖ መጣ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከኬብሮን ዘሮች፣ አለቃውን ኤሊኤልንና ሰማንያ የሥጋ ዘመዶቹን፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከኬብሮን ልጆች፤ ከሰማንያ ወንድሞቹ ጋር አለቃው ኤሊኤል ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከኬብሮን ልጆች፤ አለቃው ኢዮሔል፥ ወንድሞቹም ሰማንያ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከኬብሮን ልጆች አለቃው ኤሊኤል፥ ወንድሞቹም ሰማንያ፤ |
የእነርሱ ዘሮች የሊብናውያን ወገን፥ የኬብሮናውያን ወገን፥ የሞላውያን ወገን፥ የሙሳውያን ወገን፥ የቆሬያውያን ወገን ቀዓትም አምራምን ወለደ።