የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙት ሰዎች ስድስት እርምጃ በተራመዱ ቊጥር ዳዊት እንደገና እያስቆመ አንድ ወይፈንና አንድ የሰባ ፍሪዳ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ያቀርብ ነበር።
1 ዜና መዋዕል 15:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ዳዊት እግዚአብሔር ለዘለዓለም እርሱን እንዲያገለግሉና የቃል ኪዳኑንም ታቦት እንዲሸከሙ የመረጣቸው እነርሱን ስለ ሆነ “የቃል ኪዳኑን ታቦት መሸከም የሚገባቸው ሌዋውያን ብቻ ናቸው” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ዳዊት፣ “የእግዚአብሔርን ታቦት እንዲሸከሙና ለዘላለም በፊቱ እንዲያገለግሉ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ከሌዋውያን በቀር፣ የእግዚአብሔርን ታቦት ማንም አይሸከም” ሲል አዘዘ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜም ዳዊት እንዲህ አለ፦ “የእግዚአብሔርን ታቦት እንዲሸከሙ፥ ለዘለዓለሙም እንዲያገለግሉት ጌታ ከመረጣቸው ከሌዋውያን በቀር ማንም የጌታን ታቦት ሊሸከም አይገባውም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያን ጊዜም ዳዊት፥ “የእግዚአብሔርን ታቦት ይሸከሙ ዘንድ፥ ለዘለዓለሙም ያገለግሉት ዘንድ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ከሌዋውያን በቀር ማንም የእግዚአብሔርን ታቦት ይሸከም ዘንድ አይገባውም” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜም ዳዊት “የእግዚአብሔርን ታቦት ይሸከሙ ዘንድ፥ ለዘላለሙም ያገለግሉት ዘንድ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ከሌዋውያን በቀር ማንም የእግዚአብሔርን ታቦት ይሸከም ዘንድ አይገባውም፤” አለ። |
የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙት ሰዎች ስድስት እርምጃ በተራመዱ ቊጥር ዳዊት እንደገና እያስቆመ አንድ ወይፈንና አንድ የሰባ ፍሪዳ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ያቀርብ ነበር።
እንዲሁም ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ለለዩ፥ የመላው እስራኤል መምህራን ለሆኑ ሌዋውያን እንዲህ የሚል መመሪያ ሰጠ፦ “የተቀደሰውን የቃል ኪዳን ታቦት የዳዊት ልጅ የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን ባሠራው ቤተ መቅደስ ውስጥ አኑሩት፤ ከእንግዲህ ወዲህ እናንተ አምላካችሁን እግዚአብሔርንና ሕዝቡን እስራኤልን ማገልገል እንጂ፥ የቃል ኪዳኑን ታቦት በትከሻችሁ ተሸክማችሁ ከስፍራ ወደ ስፍራ መውሰድ የለባችሁም።
በእነርሱ ኀላፊነት የሚጠበቁት ንዋያተ ቅድሳት በትከሻቸው የሚሸከሙአቸው ስለ ሆኑ ሙሴ ለቀዓታውያን ሠረገሎችንም ሆነ በሬዎችን አልሰጣቸውም።
በዚያን ጊዜ፥ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት እንዲሸከሙ፥ በፊቱም በመቆም እንዲያገለግሉትና ሕዝቡን በእግዚአብሔር ስም እንዲባርኩ የሌዊን ነገድ በመለየት ሾመ፤ እስከ ዛሬም ድረስ የሌዊ ነገድ ትውልድ አገልግሎት ይኸው ነው።
ከዚያ በኋላ ሙሴ የእግዚአብሔርን ሕግ ጽፎ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት አገልጋዮች ለሆኑት ለሌዋውያን ካህናትና ለእስራኤል ሕዝብ አለቆች ሰጣቸው።
የሚከተለውን ትእዛዝ ሰጡ፦ “የሌዊ ዘር የሆኑት ካህናት የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ተሸክመው ሲነሡ በምታዩበት ጊዜ፥ ሰፈሩን ለቃችሁ እነርሱን ተከተሉ።