ዳዊት ከኬብሮን ወደ ኢየሩሳሌም ከመጣ በኋላ ሌሎች ተጨማሪ ሚስቶችና ቁባቶች እንዲኖሩት አደረገ። ብዙ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ተወልደውለት ነበር፤
1 ዜና መዋዕል 14:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም በኢየሩሳሌም ዳዊት ብዙ ሚስቶችን አገባ፤ ብዙ ወንዶችንና ሴቶች ልጆችንም ወለደ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት በኢየሩሳሌም ተጨማሪ ሚስቶች አገባ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ወለደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም በኢየሩሳሌም ሚስቶችን ጨምሮ አገባ ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶችን ልጆች ወለደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም በኢየሩሳሌም ሌሎች ሚስቶችን ጨምሮ አገባ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ተወለዱለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም በኢየሩሳሌም ሚስቶችን ጨምሮ ሌሎችን ወንዶችና ሴቶችን ልጆች ወለደ። |
ዳዊት ከኬብሮን ወደ ኢየሩሳሌም ከመጣ በኋላ ሌሎች ተጨማሪ ሚስቶችና ቁባቶች እንዲኖሩት አደረገ። ብዙ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ተወልደውለት ነበር፤
በዚህ ዓለም እግዚአብሔር በሰጠህ ከንቱ በሆነ ኑሮህ ከምትወዳት ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ፤ ስለ መከራህና ስለ ድካምህ ሁሉ ዋጋ ሆኖ የተሰጠህ ዕድል ፈንታ ይኸው ብቻ ስለ ሆነ ከንቱ ዘመንህን፥ እያንዳንዱን ቀን ተደሰትበት።
“ስለምን መሥዋዕታችንን አይቀበልም?” ብላችሁ ትጠይቃላችሁ፤ እግዚአብሔር መሥዋዕታችሁን የማይቀበለው የቃል ኪዳን ጓደኞቻችሁ ለሆኑት ለወጣትነት ሚስቶቻችሁ ታማኝነታችሁን ስላፈረሳችሁ ነው፤ በእናንተም መካከል እግዚአብሔር ምስክር ነበር።
እርሱም እንዲህ አላቸው፦ “ሙሴማ ሚስቶቻችሁን እንድትፈቱ የፈቀደላችሁ ልባችሁ ደንድኖ አስቸጋሪዎች በመሆናችሁ ምክንያት ነው፤ በመጀመሪያ ግን እንዲህ አልነበረም።
ደግሞም ንጉሡ ብዙ ሚስቶች እንዲኖሩት ማድረግ እግዚአብሔርን ከመከተል ስለሚገታው ንጉሡ ብዙ ሚስቶች እንዲኖሩት አያስፈልገውም፤ ወርቅና ብርም በብዛት አያከማች።