እነርሱም የቃል ኪዳኑን ታቦት በኮረብታ ላይ ከሚገኘው ከአቢናዳብ ቤት አውጥተው በአዲስ ሠረገላ ላይ አኖሩት፤ ዑዛና አሕዮ ተብለው የሚጠሩት የአቢናዳብ ልጆች ሠረገላውን እየመሩ በሚጓዙበት ጊዜ፥
1 ዜና መዋዕል 13:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቃል ኪዳኑን ታቦት ከአቢናዳብ ቤት አውጥተው በአዲስ ሠረገላ ላይ ጫኑት፤ ዑዛና አሕዮም ሠረገላውን ይነዱ ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔርንም ታቦት ከአሚናዳብ ቤት በአዲስ ሠረገላ ላይ አድርገው አመጡት፤ ሠረገላውን ይነዱ የነበሩትም ዖዛና አሒዮ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእግዚአብሔርንም ታቦት በአዲስ ሠረገላ ላይ ጫኑት፥ ከአሚናዳብም ቤት አመጡት፤ ዖዛና አሒዮም ሠረገላውን ይነዱ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርንም ታቦት ከአሚናዳብ ቤት በተገኘ በአዲስ ሰረገላ ላይ አኖሩአት። ዖዛና ወንድሞቹም ሰረገላውን ይነዱ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርንም ታቦት በአዲስ ሠረገላ ላይ ጫኑት፤ ከአሚናዳብም ቤት አመጡት፤ ዖዛና አሒዮም ሠረገላውን ይነዱ ነበር። |
እነርሱም የቃል ኪዳኑን ታቦት በኮረብታ ላይ ከሚገኘው ከአቢናዳብ ቤት አውጥተው በአዲስ ሠረገላ ላይ አኖሩት፤ ዑዛና አሕዮ ተብለው የሚጠሩት የአቢናዳብ ልጆች ሠረገላውን እየመሩ በሚጓዙበት ጊዜ፥
ከዚህም በኋላ ዳዊት እግዚአብሔር ለዘለዓለም እርሱን እንዲያገለግሉና የቃል ኪዳኑንም ታቦት እንዲሸከሙ የመረጣቸው እነርሱን ስለ ሆነ “የቃል ኪዳኑን ታቦት መሸከም የሚገባቸው ሌዋውያን ብቻ ናቸው” አለ።
ከሰፈር በሚነሡበትም ጊዜ አሮንና ልጆቹ ንዋያተ ቅድሳቱንና የእነርሱንም መገልገያ ዕቃዎች ሁሉ ከሸፈኑ በኋላ የቀዓት ልጆች መጥተው ይሸከሙአቸው፤ ነገር ግን እንዳይሞቱ ንዋያተ ቅድሳቱን መንካት አይገባቸውም፤ እንግዲህ የመገናኛው ድንኳን በሚነሣበት ጊዜ ሁሉ የቀዓት ልጆች ኀላፊነት ይህ ነው።
ስለዚህ አዲስ ሠረገላና ቀንበር ያልተጫነባቸው ሁለት ጥጆችን አዘጋጁ፤ ጥጆቹን ጠምዳችሁ ሠረገላው የሚሳብበትን ጫፍ በቀንበሩ ላይ እሰሩት፤ እንቦሶቻቸውንም ወደ በረት መልሱ፤