1 ዜና መዋዕል 12:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእነርሱም ስም በሚከተለው ሁኔታ በየማዕርጋቸው በቅደም ተከተል ተራ ተዘርዝሮአል፦ ዔዜር፥ አብድዩ ኤሊአብ፥ ሚሽማና፥ ኤርምያስ፥ ዓታይ፥ ኤሊኤል፥ ዮሐናን፥ ኤልዛባድ፥ ኤርምያስ ማክባናይ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእነዚህም አለቃ ዔጼር ነበረ፤ ሁለተኛው አዛዥ አብድዩ፣ ሦስተኛው ኤልያብ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አለቃው ዔጼር፥ ሁለተኛው አብድዩ፥ ሦስተኛው ኤልያብ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አለቃው አዝር፥ ሁለተኛው አብድያ፥ ሦስተኛው ኤልያብ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አለቃው ዔጼር፥ ሁለተኛው አብድዩ፥ ሦስተኛው ኤልያብ፥ |
ዳዊት በበረሓ በሚገኘው ምሽግ ውስጥ ሳለ ከጋድ ነገድ መጥተው ከእርሱ ሠራዊት ጋር የተባበሩት ዝነኞችና የጦር ልምድ ያላቸው ወታደሮች ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው፤ እነርሱ ጋሻና ጦር ይዘው በመዋጋት የታወቁ ነበሩ፤ አስፈሪነታቸው እንደ አንበሳ ሲሆን ፈጣንነታቸው በተራራ ላይ እንደሚዘል ሚዳቋ ነበር፤
ስለ ጋድ ነገድም እንዲህ አለ፦ “የጋድን ግዛት ያሰፋ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፤ ጋድ ክንድን ወይም ግንባርን ለመስበር፥ እንደ አንበሳ ያደባል።