La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ዜና መዋዕል 12:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነርሱም ከብንያም ነገድ ስለ ነበሩ የሳኦል ዘመዶች ነበሩ፤ እነርሱ በቀኝና በግራ እጃቸው ፍላጻ የመወርወርና ድንጋይ የመወንጨፍ ችሎታ ያላቸው ነበሩ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሰዎቹ ቀስተኞች ሲሆኑ፣ በቀኝም ሆነ በግራ እጃቸው ፍላጻ መወርወርና ድንጋይ መወንጨፍ የሚችሉ ነበሩ፤ እነርሱም ከብንያም ነገድ የሆነው የሳኦል ሥጋ ዘመዶች ነበሩ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ቀስተኞችም ነበሩ፥ በቀኝና በግራም እጃቸው ድንጋይ ሊወነጭፉ ፍላጻም ሊወረውሩ ይችሉ ነበር፤ ከብንያም ወገን የሳኦል ወንድሞች ነበሩ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ቀስ​ተ​ኞ​ችም ነበሩ፤ በቀ​ኝና በግ​ራም እጃ​ቸው ድን​ጋይ ሊወ​ነ​ጭፉ፥ ፍላ​ጻም ሊወ​ረ​ውሩ ይችሉ ነበር፤ ከብ​ን​ያም ወገን የሳ​ኦል ወን​ድ​ሞች ነበሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ቀስተኞችም ነበሩ፤ በቀኝና በግራም እጃቸው ድንጋይ ሊወነጭፉ ፍላጻም ሊወረውሩ ይችሉ ነበር፤ ከብንያም ወገን የሳኦል ወንድሞች ነበሩ።

Ver Capítulo



1 ዜና መዋዕል 12:2
7 Referencias Cruzadas  

እነርሱ የጊብዓ ተወላጅ የሆነው የኢሸማዓ ልጆች በሆኑት በአሒዔዜርና በዮአሽ አመራር ሥር ነበሩ። የወታደሮቹም ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፦ የዓዝማዌት ልጆች ይዚኤልና ፔሌጥ፥ የዐናቶት ተወላጆች የሆኑት በራካና ኢዩ፥ ዝነኛ ወታደር የነበረው፥ በኋላም የሠላሳዎቹ ኀያላን መሪዎች ከሆኑት አንዱ የሆነው፥ የገባዖን ተወላጅ ዩሽማዕያ፥ የገዴራ ተወላጆች የሆኑት ይርመያ፥ ያሕዚኤል፥ ዮሐናንና ዮዛባድ፥ የሐሪፍ ተወላጆች የሆኑት ኤልዑዛይ፥ ያሪሞት፥ በዓልያ፥ ሸማርያና ሸፋጥያ፥ ከቆሬ ጐሣዎች የሆኑት ኤልቃና፥ ዩሺያሁ፥ ዐዛርኤል፥ ዮዔዜርና ያሸብዓም፥ የገዶር ተወላጆች የሆኑት የይሮሐም ልጆች ዮዔላና ዘባድያ።


የኡላም ወንዶች ልጆች ዝነኛ ወታደሮችና ቀስት ወርዋሪዎች ነበሩ፤ የእነርሱም ዘሮች በአጠቃላይ አንድ መቶ ኀምሳ ልጆችና የልጅ ልጆች ነበሩ፤ እንግዲህ ከዚህ በላይ ስሞቻቸው የተጠቀሱት ሁሉ የብንያም ነገድ ነበሩ።


የኤፍሬም ልጆች ቀስትና ፍላጻ ይዘው ሳለ በጦርነት ቀን ሸሹ።


ከእነዚያም መካከል የተመረጡ ሰባት መቶ ግራኝ ሰዎች ነበሩ፤ እነዚህም ድንጋይ የሚወነጭፉና ሌላው ቀርቶ አንዲት ጠጒርን እንኳ የማይስቱ ነበሩ።


ከዚህ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እግዚአብሔርም ከብንያም ነገድ ግራኝ የነበረውን የጌራን ልጅ ኤሁድን አዳኝ አድርጎ አስነሣቸው፤ የእስራኤል ሕዝብ ኤሁድን ግብር አስይዘው ወደ ሞአብ ንጉሥ ወደ ዔግሎን ላኩት።


እጁንም ወደ ኮረጆው ከቶ አንዲት ድንጋይ በማውጣት በጎልያድ ላይ ወነጨፈ፤ ድንጋዩም ግንባሩን በጥርቆ ወደ ራስ ቅሉ ገባ፤ ጎልያድም በምድር ላይ በግንባሩ ተደፋ።