1 ዜና መዋዕል 11:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን ሁሉ በኬብሮን ወደነበረው ወደ ዳዊት ሄደው እንዲህ አሉት፦ “እኛ ሁላችን የሥጋ ዘመዶችህ ነን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤል ሁሉ በኬብሮን ወደ ዳዊት ተሰብስበው እንዲህ አሉ፤ “እነሆ፤ እኛ የዐጥንትህ ፍላጭ፣ የሥጋህ ቍራጭ ነን፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤልም ሁሉ በኬብሮን ወደ ዳዊት ተሰብስበው እንዲህ አሉት፦ “እነሆ፥ እኛ የአጥንትህ ፍላጭ የሥጋህ ቁራጭ ነን፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስራኤልም ሁሉ በኬብሮን ወደ ዳዊት ተሰብስበው እንዲህ አሉት፥ “እነሆ፥ እኛ የአጥንትህ ፍላጭ የሥጋህ ቍራጭ ነን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤልም ሁሉ በኬብሮን ወደ ዳዊት ተሰብስበው “እነሆ፥ እኛ የአጥንትህ ፍላጭ የሥጋህ ቍራጭ ነን፤ |
“ነገር ግን ወደ እስራኤል ነገዶች ሁሉ መልእክተኞችን ልኮ የእምቢልታ ድምፅ በምትሰሙበት ጊዜ ድምፃችሁን ከፍ በማድረግ ‘አቤሴሎም የኬብሮን ንጉሥ ሆኗል!’ ብላችሁ ጩኹ” ብለው እንዲነግሩአቸው አደረገ።
ከዚህ በኋላ ዳዊት ከይሁዳ ከተሞች ወደ አንድዋ ልውጣን? ሲል እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም “አዎ ውጣ” አለው። ዳዊትም “ወደ የትኛይቱ ከተማ ልሂድ?” ሲል ጠየቀ። እግዚአብሔርም “ወደ ኬብሮን ከተማ ሂድ” አለው።
በመጀመሪያው ወደ ኔጌብ ሄደው ወደ ኬብሮን መጡ፤ ይህችም ኬብሮን “ዐናቂም” ተብለው የሚጠሩ የግዙፋን ሰዎች ዘር የሆኑ አሒማን፥ ሼሻይ እና ታልማይ የሚባሉት ጐሣዎች መኖሪያ ነበረች። (ኬብሮን የተመሠረተችውም በግብጽ ምድር ጾዓን ተብላ የምትጠራው ከተማ ከመቈርቈርዋ ሰባት ዓመት ቀደም ብሎ ነበር።)
እግዚአብሔር አምላክህ የሚመርጥልህን ንጉሥ ልታነግሥ ትችላለህ፤ በአንተም ላይ የምታነግሠው ንጉሥ ከወገንህ መካከል ይሁን፥ ከወገንህ ያልሆነውን የውጪ አገር ሰው ልታነግሥ አይገባህም።
“ለሴኬም ሰዎች ሁሉ እንዲህ ብላችሁ ንገሩአቸው፦ ‘የጌዴዎን ሰባ ልጆች፥ ወይስ አንድ ሰው ብቻ ቢገዛችሁ ይሻላል? እኔ ደግሞ ለእናንተ የአጥንታችሁ ፍላጭ የሥጋችሁ ቊራጭ መሆኔን አስታውሱ።’ ”