1 ዜና መዋዕል 1:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የከነዓን የበኲር ልጅ ጺዶን ሲሆን እንዲሁም ሒታውያን፥ ኢያቡሳውያን፥ አሞራውያን፥ ጌርጌሳውያን፥ ሒዋውያን፥ ዓርቃውያን፥ ሲናውያን፥ አርዋዳውያን፥ ጸማራውያንና ሐማታውያን የከነዓን ልጆች ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከነዓንም፦ የበኵር ልጁ የሲዶን፣ የኬጢያውያን፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከነዓንም የወለደው የበኩር ልጁን ሲዶንን፥ ሔትን፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከነዓን የበኵር ልጁን ሲዶንን፥ ኬጤዎንን፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከነዓንም የበኵር ልጁን ሲዶንን፥ ኬጢን፥ |
ርብቃ ይስሐቅን “ዔሳው ባገባቸው በእነዚህ በሒታውያን ሴቶች ምክንያት መኖሬን ጠላሁት፤ ያዕቆብ ደግሞ ከነዚህ ከሒታውያን ሴቶች አንዲቱን ካገባ ከመኖር ይልቅ ሞቴን እመርጣለሁ” አለችው።
ከዮርዳኖስ ማዶ በተራራማውና በቈላማው አገሮች፥ በሜዲቴራኒያን ባሕር ጠረፍ፥ እስከ ሊባኖስ ድረስ ያሉት የሒታውያን፥ የአሞራውያን፥ የከነዓናውያን፥ የፔሩዛውያን የኤዊያውያንና የኢያቡሳውያን ነገሥታት ይህን በሰሙ ጊዜ፥