እኔን እንድትረዳኝ፥ ከእኔ ጋር እንድትደክም፥ አንተን የሚያስደስትህን እንድታስምረኝ፥ ከቅዱሳን ሰማያት አውጣት፤ ከከበረው ዙፋንህም ወደዚህ ላካት።
ተነሥታ ትመጣ ዘንድ ከከበሩ ሰማዮች ከጌትነትህ ዙፋን ወደኔ ላካት፤ ከእኔም ጋራ ትኖርና ትደክም ዘንድ ደስ የሚያሰኝህም ምን እንደ ሆነ ዐውቅ ዘንድ ላካት።