አእምሮ የሌላቸውንና የሚሳቡትን፥ የተጠሉትን ጢንዚዛዎች እስከማምለክ ባደረሳቸውና ከመንገድ ባወጣቸው ሞኝነታቸውና ክፉ ሐሳባቸው ምክንያት ልትቀጣቸው አእምሮ የሌላቸውን የእንስሳት መንጋ ላክህባቸው።
ዳግመኛም በክፋት ቀድሞ የጣሉትን አጡት፤ ከዚህም በኋላ በመዘባበት ከእርሱ ሸሹ፤ ከትእዛዙ መውጣት ፍጻሜ የተነሣም አደነቁ፥ ጻድቃንም እንደ ተጠሙ እነርሱ የተጠሙ አይደሉም።