ማሕልየ መሓልይ 6:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንቺ ሱላማጢስ ሆይ። ተመለሽ፥ ተመለሽ፥ እናይሽ ዘንድ ተመለሽ፥ ተመለሽ። በሱላማጢስ ምን ታያላችሁ? እርሷ እንደ መሃናይም ዘፈን ናት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንቺ ሱላማጢስ ሆይ፤ ተመለሺ፤ ኧረ ተመለሺ፤ እንድናይሽ ተመለሺ፤ እባክሽ ተመለሺ። የመሃናይምን ዘፈን እንደሚመለከት ሰው፣ ሱላማጢስን የምትመለከቷት ለምንድን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንቺ ሱላማዊት ሆይ! ነዪ ተመለሺ፤ በደንብ አድርገን እንድንመለከትሽ ነዪ ተመለሺ። ሱላማጢስን በሁለት ሠራዊት መካከል እንደሚደረግ ጭፈራ የምትመለከቱአት ለምንድን ነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያ ጡቶችን እሰጥሃለሁ፥ ሰውነቴም አላወቀችም፥ እንደ አሚናዳብ ሰረገላ አደረገኝ አለች። |
ፀሐይ መልኬን አክስሎታልና ጥቁር ስለ ሆንኩ አትዩኝ፥ የእናቴ ልጆች ተጣሉኝ፥ የወይን ቦታዎችንም ጠባቂ አደረጉኝ፥ ነገር ግን የእኔን ወይን ቦታ አልጠበቅሁም።
ወደ ሴቲቱም ዘወር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፦ “ይህችን ሴት ታያለህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፤ ውሃ እንኳ ለእግሬ አላቀረብህልኝም፤ እርሷ ግን በእንባዋ እግሬን አራሰች፤ በጠጉርዋም አበሰች።
ይህም የሚሆነው ምስክርነታችን በእናንተ በመታመኑ የተነሣ ባመኑት ሁሉ ዘንድ ሊደነቅና፥ በቅዱሳኑም ሊከብር በሚመጣበት ጊዜ በዚያ ቀን ነው።
ለእርሱም አብርሃም ከሁሉ ከዐሥር አንድ ሰጠው፥፥ የስሙ ትርጓሜ በመጀመሪያ፥ የጽድቅ ንጉሥ ነው፤ ከዚያ ደግሞ፥ የሳሌም ንጉሥ ማለት የሰላም ንጉሥ ነው።
አድፍጣችሁ ተጠባበቁ። የሴሎ ልጃገረዶች ለጭፈራ ወደዚያ በሚወጡበት ጊዜ፥ ከወይኑ አትክልት ቦታ ወጥታችሁ ከልጃገረዶቹ ለየራሳችሁ ሚስት ጥለፉ፤ ወደ ብንያምም ምድር ሂዱ።