እግዚአብሔርን ፍራ፤ ካህንን አክብር፤ እንደታዘዝኸው ድርሻውን ስጠው፤ የምትሰጠውም ከእህሉ የመጀመሪያውን ስለ ኃጢአት ካሣ የሚሠዋውን መሥዋዕት፥ ወርቹን፥ የመቀደሻውን መሥዋዕት ከተቀደሱት ነገሮች የመጀመሪያውን ነው።
እግዚአብሔርን ፍራው፤ የሚያገለግለውን ካህኑንም አክብረው፤ የታዘዘልህ ዕድሉንም ስጠው፤ ቀዳምያቱንና፥ ስለ ኀጢአት የሚሠዋውን መሥዋዕት፥ ወርቹንም፥ ማታና ጧትም የሚሠዋውን መሥዋዕት፥ መጀመሪያ የሚወለደውንም ከብት ስጠው።