ለማረፍ እንደተጋደመ ብዙም ሳይቆይ፥ እንደ ቀኑ ሁሉ በእንቅልፍ ልቡም ቅዠቶች ያስጨንቁታል፤ ከጦርነት እንዳመለጠ፥
ዕረፍቱ ጥቂት ወይም እንደ ኢምንት ነው፤ ይህ ሁሉ በመኝታው ይታወቃል፤ አንድ ጊዜ እንደ ሸንጎ ተከማችቶ ያገኘዋል፤ ከሰልፍ እንደሚሸሽ ሰውም የልቡናውን ምክር ያወላውላታል።