በቃል ኪዳንህ፥ በቤተ መቅደስህ፥ በጽዮን ተራራና ልጆችህ በወረሱት ቤት ላይ የጥፋት ትልሞች የነደፉትን ሁሉ የሚያታልሉ ቃላቶቼ እንዲያቆስላቸውና እንዲያጠፋቸው አድርግ።
የቃሌንም ጥበብ በሕግህና በቤተ መቅደስህ በደብረ ጽዮንና በልጆችህ ንብረት ቤት ላይ ክፉ ነገርን የመከሩ ጠላቶችን እንዲያቈስላቸውና እንዲያጠፋቸው አድርግ።