በየድንኳኑ ስለ ዮዲት መምጣት ተወርቶ ነበርና በሰፈሩ ሁሉ ታላቅ መደነቅ ሆነ፥ መምጣቷንም እስኪነግሩላት ድረስ ከሆሎፎርኒስ ድንኳን ውጭ ቆማ በመጠበቅ ላይ ሳለች ሰዎች በዙሪያዋ ተሰበሰቡ።
ሕዝቡም ሁሉ ተሰበሰቡ፤ በድንኳኑ ፊት እንዳለች ዜናዋ በሰፈሩ ተሰምቶ ነበርና መጥተው ስለ እርሷ እስኪነግሩት ድረስ ከሆሎፎርኒስ ድንኳን ውጭ ከብበዋት ቆሙ።