መጽሐፈ ዮዲት 10:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ የመጣሁት የሠራዊቶቻችሁ ዋና የጦር አዛዥ የሆነውን ሆሎፎርኒስን ለማግኘትና ለእርሱ እውነተኛ ነገርን ለመንገር ነው፤ ከሰዎቹ አንድም ሳይሞትበት ተራራማውን አገር በሙሉ መያዝ እንዲችል መከተል የሚገባውን መንገድ አሳየዋለሁ”። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ እውነተኛ ነገርን እነግረው ዘንድ፥ የምትሄዱበትንም ጎዳና አሳየው ዘንድ ወደ ቢትወደዳችሁ ወደ ሆሎፎርኒስ አስቀድሜ መጣሁ፤ አውራጃቸውንም ሁሉ ገንዘብ ታደርጋላችሁ፤ ከሰዎቻችሁ አንድ ሰው ስንኳ የሚቈስል የለም።” |