ሕዝቅኤል 46:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ውጭው አደባባይ አወጣኝ በአደባባይም ወዳለው ወደ አራቱ ማዕዘን አዞረኝ፤ እነሆ በእያንዳንዱ የአደባባይ ማዕዘን አደባባይ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ወደ ውጩ አደባባይ አመጣኝ፤ በአራቱም ማእዘን ዙሪያ መራኝ፤ በእያንዳንዱም ማእዘን ሌላ አደባባይ አየሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ ያ ሰው ወደ ውጪው አደባባይ አምጥቶ በአራቱ ማእዘን አዞረኝ፤ በያንዳንዱም ማእዘን አንድ አደባባይ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውጭው አደባባይ አወጣኝ፤ በአደባባይም ወዳለው ወደ አራቱ ማዕዘን አዞረኝ፤ እነሆም፥ በአደባባዩ ማዕዘን ሁሉ አደባባይ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውጭው አደባባይ አወጣኝ በአደባባይም ወዳለው ወደ አራቱ ማዕዘን አዞረኝ፥ እነሆም፥ በአደባባዩ ማዕዘን ሁሉ አደባባይ ነበረ። |
እንዲህም አለኝ፦ “ካህናቱ ሕዝቡን ለመቀደስ ወደ ውጭው አደባባይ እንዳያወጡ የበደሉን መሥዋዕትና የኃጢአቱን መሥዋዕት የሚቀቅሉበት፥ የእህሉንም ቁርባን የሚጋግሩበት ስፍራ ይህ ነው።”