ሕዝቅኤል 44:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መበለቲቱንና የተፈታችውን ለሚስትነት አይውሰዱ፤ነገር ግን ከእስራኤል ቤት ዘር የሆነችውን ድንግል ወይም የካህን ሚስት የነበረችውን መበለት ይውሰዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መበለቶችን ወይም ፈት ሴቶችን አያግቡ፤ ነገር ግን ከእስራኤል ዘር የሆኑ ድንግሎችን ወይም የካህናት ሚስቶች የነበሩትን መበለቶች ማግባት ይችላሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህን የሆነ ሁሉ ባልዋ የሞተባትን ወይም ከባልዋ የተፋታችውን ሴት ማግባት አይፈቀድለትም፤ ነገር ግን ድንግል የሆነችውን እስራኤላዊት ልጃገረድ ወይም ካህን የሆነ ባልዋ የሞተባትን ሴት ማግባት ይችላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መበለቲቱንና የተፈታችይቱን አያግቡ፤ ከእስራኤል ቤት ዘር ግን ድንግሊቱን ወይም የካህን ሚስት የነበረችይቱን መበለት ያግቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መበሊቲቱንና የተፈታችይቱን አያግቡ፥ ከእስራኤል ቤት ዘር ግን ድንግሊቱን ወይም የካህን ሚስት የነበረችይቱን መበለት ያግቡ። |
እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል፤ ነቀፋ የሌለበት፥ የአንዲት ሚስት ባል፥ በመጠን የሚኖር፥ ራሱን የሚቈጣጠር፥ በሥርዓት የሚሠራ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር ብቃት ያለው፥