ሕዝቅኤል 44:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ውጭው አደባባይ ወደ ሕዝቡ በሚወጡበት ጊዜ ያገለገሉበትን ልብሳቸውን ያውልቁ፥ በተቀደሰው ቤት ውስጥ ያኑሩት፥ ሕዝቡንም በልብሳቸው እንዳይቀድሱ ሌላ ልብስ ይልበሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡ ወዳለበት ወደ ውጩ አደባባይ ሲወጡ፣ ሲያገለግሉበት የነበረውን ልብስ አውልቀው በተቀደሱት ክፍሎች በመተው ሌሎች ልብሶችን ይልበሱ፤ ይኸውም ሕዝቡን በልብሳቸው እንዳይቀድሱ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡ ወደሚገኙበት ወደ ውጪው አደባባይ ከመውጣታቸው በፊት በቤተ መቅደስ ለአገልግሎት የተጠቀሙባቸውን አልባሳት አውልቀው በተቀደሱት ዕቃ ቤቶች ማኖርና ለራሳቸውም ሌላ ልብስ መልበስ አለባቸው፤ ይህንንም የሚያደርጉት ሕዝቡ ያልተፈቀደለትን የእነርሱን የተቀደሰ ልብስ ነክቶ እንዳይጐዳ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ውጭውም አደባባይ ወደ ሕዝብ በወጡ ጊዜ ያገለገሉበትን ልብሳቸውን ያውልቁ፤ በተቀደሰውም ዕቃ ቤት ውስጥ ያኑሩት፤ ሕዝቡንም በልብሳቸው እንዳይቀድሱ ሌላውን ልብስ ይልበሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ውጭውም አደባባይ ወደ ሕዝብ በወጡ ጊዜ ያገለገሉበትን ልብሳቸውን ያውልቁ በተቀደሰውም ዕቃ ቤት ውስጥ ያኑሩት፥ ሕዝቡንም በልብሳቸው እንዳይቀድሱ ሌላውን ልብስ ይልበሱ። |
እንዲህም አለኝ፦ “ካህናቱ ሕዝቡን ለመቀደስ ወደ ውጭው አደባባይ እንዳያወጡ የበደሉን መሥዋዕትና የኃጢአቱን መሥዋዕት የሚቀቅሉበት፥ የእህሉንም ቁርባን የሚጋግሩበት ስፍራ ይህ ነው።”
የተቀደሰውን የበፍታ ቀሚስ ይልበስ፥ የበፍታውም ሱሪ በገላው ላይ ይሁን፥ በመርገፍም የተጌጠውን የበፍታው መታጠቂያ ይታጠቅ፥ የበፍታውንም መጠምጠሚያ ይጠምጥም፤ እነዚህ የተቀደሱ ልብሶች ናቸው፤ ገላውንም በውኃ ታጥቦ ይልበሳቸው።
እርሱም ኃጢአትን ሠርቶ በደለኛ ቢሆን፥ በቅሚያ የወሰደውን ወይም በግፍ የተቀበለውን ወይም በአደራ ከእርሱ ዘንድ የተቀመጠውን ወይም ጠፍቶ ያገኘውን፥
አንድ ሰው የተቀደሰ ሥጋ በልብሱ ዕጥፋት ቢይዝ፥ ዕጥፋቱ እንጀራ ወይም ወጥ፥ ወይም የወይን ጠጅ፥ ወይም ዘይት፥ ወይም ማናቸውንም መብል ቢነካ ያ የተነካው የተቀደሰ ይሆናልን? ካህናቱም፦ አይሆንም ብለው መለሱ።