ሕዝቅኤል 36:37 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አሁንም የእስራኤል ቤት እንድሠራላቸው እንዲፈልጉኝ እፈቅድላቸዋለሁ፥ ሰዎችንም እንደ መንጋ አበዛላቸዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እንደ ገና ለእስራኤል ቤት ልመና ዕሺ እላለሁ፤ ይህንም አደርግላቸዋለሁ፤ ሕዝባቸውን እንደ በግ መንጋ አበዛዋለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እስራኤላውያን ደግመው አንድ ጊዜ ይህን እንዲለምኑኝ አደርጋለሁ፤ ቊጥራቸውንም እንደ በጎች መንጋ አበዛዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለዚህ ደግሞ አደርግላቸው ዘንድ የእስራኤል ቤት ይሹኛል፤ ሰውንም እንደ መንጋ አበዛላቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለዚህ ደግሞ አደግላቸው ዘንድ የእስራኤል ቤት ይሹኛል ሰውንም እንደ መንጋ አበዛላቸዋለሁ። |
የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ ሰዎች ጣዖቶቻቸውን በልባቸው አኑረዋል። የበደላቸውንም የማሰናከያ ድንጋይ በፊታቸው አስቀምጠዋል፥ ታዲያ እንዲጠይቁኝ ልፍቀድላቸው?
የሰው ልጅ ሆይ፥ የእስራኤልን ሽማግሌዎች ተናገራቸው፥ እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እናንተ እኔን ልትጠይቁ መጣችሁን? እኔ ሕያው ነኝ፥ ለእናንተ አልጠየቅም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ቁርባናችሁን ባቀረባችሁ ጊዜ፥ ልጆቻችሁንም በእሳት ባሳለፋችሁ ጊዜ፥ እስከ ዛሬ ድረስ በጣዖቶቻችሁ ትረክሳላችሁን የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ከእናንተስ ዘንድ እጠየቃለሁን? እኔ ሕያው ነኛና ከእናንተ ዘንድ አልጠየቅም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤
በዙሪያችሁም የቀሩት መንግሥታት፥ የፈረሱትን ስፍራዎች የሠራሁ፥ ባድማ የሆነውንም የተከልሁ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ፤ እኔ ጌታ ተናግሬአለሁ፥ እኔም አደርገዋለሁ።
እንደ ተቀደሰ መንጋ፥ በበዓላቶችዋ ቀን እንደሚሆኑ እንደ ኢየሩሳሌም መንጋ፥ እንዲሁም የፈረሱት ከተሞች በሰዎች መንጋ ይሞላሉ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።
ያዕቆብ ሆይ፥ ሁላችሁንም ፈጽሞ እሰበስባለሁ፥ የእስራኤልን ትሩፍ በአንድ ላይ እሰበስባለሁ፤ በጋጣ ውስጥ እንዳሉ በጎች፥ በማሰማርያው ውስጥ እንዳለ መንጋ አደርገዋለሁ፤ ከሰው ብዛት የተነሣ ድምፃቸውን ያሰማሉ።
የይሁዳን ቤት አበረታለሁ፥ የዮሴፍንም ቤት አድናለሁ፤ ስለምራራላቸው ወደ ቦታቸው እመልሳቸዋለሁ፤ እነርሱም በእኔ እንዳልተተዉ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው ጌታ ነኝና፥ እኔም እሰማቸዋለሁ።
አንድ ሦስተኛውን ክፍል ወደ እሳት አስገባለሁ፤ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፤ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፤ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፤ እኔም፦ “ይህ ሕዝቤ ነው” እላለሁ፥ እርሱም፦ “ጌታ አምላኬ ነው” ይላል።