ሕዝቅኤል 34:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ውጭ እስክትበትኑአቸው ድረስ በጎንና በትከሻ ስለምትገፉ፥ የደከሙትን ሁሉ በቀንዳችሁ ስለምትወጉአቸው፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደካሞቹን በጎች በጐናችሁና በትከሻችሁ ስለምትገፈትሩ፣ እስኪባረሩም ድረስ በቀንዳችሁ ስለምትወጓቸው፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ በጎናችሁና በትከሻችሁ እየገፈተራችሁ ደካሞችን እንስሶች በቀንዳችሁ ወግታችሁ ወደ ሩቅ ቦታ ታባርሩአቸዋላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስክትበትኑአቸው ድረስ በእንቢያና በትከሻ ስለምትገፉአቸው፥ የደከሙትንም ሁሉ በቀንዳችሁ ስለምትወጉአቸው፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስክትበትኑአቸው ድረስ በእንቢያና በትከሻ ስለምትገፉአቸው የደከሙትንም ሁሉ በቀንዳችሁ ስለምትወጉአቸው፥ |
እናንተም ድሀውን ረግጣችኋልና፥ የስንዴውንም ቀረጥ ከእርሱ ወስዳችኋልና፥ ከተጠረበ ድንጋይ ቤቶችን ሠርታችኋል፥ ነገር ግን አትቀመጡባቸውም፤ ያማሩ የወይን ቦታዎች ተክላችኋል፥ ነገር ግን ከወይን ጠጃቸው አትጠጡም።
እጆቻቸው ክፉ ለማድረግ የተለማመዱ ናቸው፤ ልዑሉና ፈራጁ ጉቦን ይፈልጋሉ፥ ትልቁም ሰው እንደ ነፍሱ ምኞት ይናገራል፤ እንዲሁም ክፋትን ይጐነጉናሉ።
የገዙአቸው ያርዱአቸዋል፥ እንደ በደለኞች አይቆጠሩም፥ የሸጧቸውም፦ “ባለ ጠጋ ሆኛለሁ፤ ጌታ ይመስገን!” ይላሉ። እረኞቻቸው እንኳን አይራሩላቸውም።
ለላሞች በኩር ግርማ ይሆናል፥ ቀንዶቹ አንድ ቀንድ እንዳለው ናቸው፥ በእነርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ያሉትን አሕዛብ ሁሉ ይወጋል፥ የኤፍሬም እልፍ አእላፋት፥ የምናሴም አእላፋት እነርሱ ናቸው።”