ሕዝቅኤል 33:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኃጢአተኛውም ከኃጢአቱ ተመልሶ ፍርድንና ቅን ነገርን ቢያደርግ በእነርሱ በሕይወት ይኖርበታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉም ሰው ከክፉ ሥራው ተመልሶ ቀናውንና ትክክለኛውን ቢያደርግ፣ ይህን በማድረጉ በሕይወት ይኖራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉም ሰው ኃጢአት መሥራትን ትቶ እውነተኛና ትክክለኛ የሆነውን ነገር ቢያደርግ በእርሱ ይኖራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀጢአተኛውም ከኀጢአቱ ተመልሶ ፍርድንና ጽድቅን ቢያደርግ በሕይወት ይኖርበታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኃጢአተኛውም ከኃጢአቱ ተመልሶ ፍርድንና ቅን ነገርን ቢያደርግ በሕይወት ይኖርበታል። |
አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ የሕዝብህን ልጆች እንዲህ በላቸው፦ በበደለበት ቀን የጻድቅ ጽድቁ አያድነውም፥ ኃጢአተኛም ከኃጢአቱ በተመለሰበት ቀን በኃጢአቱ አይሰናከልም፤ ጻድቁም ኃጢአት በሠራበት ቀን በጽድቁ በሕይወት አይኖርም።