እናንተ የጊልቦዓ ተራሮች ሆይ፤ በዚያ የኀያሉ ሰው ጋሻ ረክሶአልና፤ የሳኦል ጋሻ በዘይት መወልወሉ ቀርቶአልና፤ ጠልም ሆነ ዝናብ አይውረድባችሁ፤ የቁርባን እህል የሚያበቅሉም እርሻዎች አይኑራችሁ።
ሕዝቅኤል 31:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ሲኦል በወረደበት ቀን ልቅሶ አስለቀስሁ፥ ቀላዩን ስለ እርሱ ሸፈንሁት፥ ፈሳሾቹን ገታሁ፥ ታላላቆችም ውኆች ተከለከሉ፤ ሊባኖስንም ስለ እርሱ አሳዘንሁት፥ የዱርም ዛፎች ሁሉ ስለ እርሱ ዛሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ወደ መቃብር በወረደበት ቀን ጥልቅ ምንጮችን ስለ እርሱ በሐዘን ሸፈንኋቸው፤ ወንዞቹን ገታሁ፤ ታላላቅ ፈሳሾችም ተቋረጡ። በርሱም ምክንያት ሊባኖስን ጨለማ አለበስሁ፤ የደን ዛፎችም ሁሉ ደረቁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልዑል እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ “ያ ዛፍ ተቈርጦ ወደ ሙታን ዓለም በሚወርድበት ጊዜ ጥልቁን ውሃ ዘግቼ እየተለቀሰለት ይሸፈናል። ወንዞችም እንዲቋረጡ አደርጋለሁ፤ ኀይለኞቹ ወራጅ ውሃዎችም እንዲቆሙ ይደረጋሉ። በዚህም ምክንያት በሊባኖስ ተራራዎች ላይ የጨለማ ግርዶሽ አመጣለሁ፤ ስለዚህም የሜዳ ዛፎች ሁሉ ይጠወልጋሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ሲኦል በወረደበት ቀን ልቅሶን አስለቀስሁ፤ ቀላዩንም ስለ እርሱ ሸፈንሁት፤ ፈሳሾችንም ከለከልሁ፤ ታላላቆችም ውኆች ተከለከሉ፤ ሊባኖስንም ስለ እርሱ አሳዘንሁት። የዱርም ዛፎች ሁሉ ስለ እርሱ ዛሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ሲኦል በወረደበት ቀን ልቅሶ አስለቀስሁ፥ ቀላዩንም ስለ እርሱ ሸፈንሁት ፈሳሾቹንም ከለከልሁ ታላላቆችም ውኆች ተከለከሉ፥ ሊባኖስንም ስለ እርሱ አሳዘንሁት፥ የዱርም ዛፎች ሁሉ ስለ እርሱ ዛሉ። |
እናንተ የጊልቦዓ ተራሮች ሆይ፤ በዚያ የኀያሉ ሰው ጋሻ ረክሶአልና፤ የሳኦል ጋሻ በዘይት መወልወሉ ቀርቶአልና፤ ጠልም ሆነ ዝናብ አይውረድባችሁ፤ የቁርባን እህል የሚያበቅሉም እርሻዎች አይኑራችሁ።
በዚያን ጊዜ የባሕር አለቆች ሁሉ ከዙፋኖቻቸው ይወርዳሉ፤ መጐናጸፊያቸውን ያስቀምጣሉ፥ ወርቀዘቦ ልብሳቸውንም ያወልቃሉ፤ መንቀጥቀጥን ይለብሳሉ፥ በመሬት ላይ ይቀመጣሉ፥ ሁልጊዜም ይንቀጠቀጣሉ፥ በአንቺም ይደነቃሉ።