ሕዝቅኤል 29:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያ ቀን ለእስራኤል ቤት ቀንድን አበቅላለሁ፥ ለአንተ ደግሞ በመካከላቸው የተከፈተ አፍን እሰጥሃለሁ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በዚያ ቀን ለእስራኤል ቤት ቀንድ አበቅላለሁ፤ በመካከላቸውም አፍህን እከፍታለሁ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ይህ በሚሆንበት ጊዜ የእስራኤልን ሕዝብ አበረታለሁ፤ አንተም ሕዝቅኤል ሆይ! ሰዎች ሊያደምጡህ በሚችሉበት ቦታ ሁሉ ድምፅህን ከፍ አድርገህ እንድትናገር አደርግሃለሁ፤ በዚህም ሁኔታ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በዚያ ቀን ለእስራኤል ቤት ቀንድን አበቅላለሁ፤ በመካከላቸውም ለአንተ የተከፈተ አፍን እሰጥሀለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያ ቀን ለእስራኤል ቤት ቀንድን አበቅላለሁ፥ በመካከላቸውም ለአንተ የተከፈተ አፍን እሰጣለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደሆንሁ ያውቃሉ። |
“እነሆ፥ ለዳዊት ጻድቅ ቁጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ፥ እርሱም ንጉሥ ሆኖ ይነግሣል፥ ይከናወንለታልም፥ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል።
በዚያን ቀን አፍህ ላመለጠው ሰው ይከፈታል፥ ትናገራለህም፥ ከዚያ በኋላም ድዳ አትሆንም። ስለዚህ ምልክት ትሆናቸዋለህ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።
ከእንግዲህ ወዲያ ለእስራኤል ቤት መታመኛ አይሆንም፥ እነርሱን በተከተሉ ጊዜ በደልን ያሳስባል፤ እኔም ጌታ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ያውቃሉ።
ነገር ግን በተናገርሁህ ጊዜ አፍህን እከፍታለሁ፥ አንተም እንዲህ ትላቸዋለህ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ የሚሰማ ይስማ፥ የማይሰማም አይስማ፥ እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና።
ያመለጠው ሰው ከመምጣቱ በፊት በነበረው ምሽት የጌታ እጅ በእኔ ላይ ነበረች፥ በነጋውም ወደ እኔ እስኪመጣ ድረስ አፌን ከፈተ፤ አፌም ተከፈተ ከዚያም በኋላ ዲዳ አልሆንሁም።
ጌታ! እርሱን የሚቃወሙ ይደቅቃሉ፥ ከሰማይም ያንጐደጉድባቸዋል፥ ጌታ እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል፥ ለንጉሡም ኃይል ይሰጣል፥ የመሢሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።”