እንዲያውም ሠራዊት እንዲያሰባስብ፤ የጦር መሣሪያ እንዲሠራ፥ የጦር ጓደኛው ነኝ እንዲል ሥልጣን ሰጠው፤ በኢየሩሳሌም ምሽግ ውስጥ በዋስትና የተያዙበት ሰዎች እንዲመለሱለትም አዘዘ።