ዘኍል 9:16 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁ ሁልጊዜ ነበረ፤ በቀን ደመና በሌሊትም የእሳት አምሳል ይሸፍነው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህ በዚህ ሁኔታ ቀጠለ፤ ደመናው ማደሪያውን ሸፈነው፤ በሌሊትም የእሳት መልክ ነበረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁልጊዜ በማደርያው ላይ እንዲሁ ነበረ፤ በቀን ደመና በሌሊትም የእሳት አምሳል ይሸፍነው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቀን ደመና ይሸፍነው ነበር፤ ደመናውም በሌሊት እንደ እሳት ያበራ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁ ሁልጊዜ ነበረ፤ በቀን ደመና፥ በሌሊትም የእሳት አምሳል ይሸፍናት ነበር። |
አንተ በምሕረትህ ብዛት በምድረ በዳ አልተውሃቸውም፥ በመንገድም ይመራቸው ዘንድ የደመና ዓምድ በቀን፥ የሚሄዱበትንም መንገድ ያበራላቸው ዝነድ የእሳት ዓምድ በሌሊት ከእነርሱ አልራቀም።
ታላቅም ድምፅ ከሰማይ፦ እነሆ፥ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው ከእነርሱም ጋር ያድራል፥ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል፤