ዘኍል 8:21 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሌዋውያንም ከኃጢአት ተጣጠቡ፥ ልብሳቸውንም አጠቡ፤ አሮንም ስጦታ አድርጎ በእግዚአብሔር ፊት አቀረባቸው፥ አሮንም ያነጻቸው ዘንድ አስተሰረየላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌዋውያኑ ራሳቸውን አነጹ፤ ልብሶቻቸውንም ዐጠቡ፤ ከዚያም አሮን እንደሚወዘወዝ መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት አቀረባቸው፤ እንዲነጹም ማስተስረያ አደረገላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌዋውያንም ከኃጢአት ራሳቸውን አነጹ፥ ልብሳቸውንም አጠቡ፤ አሮንም ለመወዝወዝ ቁርባን በጌታ ፊት አቀረባቸው፥ አሮንም እነርሱን ለማንጻት ማስተስረያ አደረገላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌዋውያንም ራሳቸውን አነጹ፤ ልብሳቸውንም አጠቡ፤ አሮንም ለእግዚአብሔር ልዩ ስጦታ አድርጎ ለእግዚአብሔር ለያቸው የመንጻቱንም ሥርዓት ፈጸመላቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሌዋውያንም ከኀጢአት ራሳቸውን አነጹ፤ ልብሳቸውንም አጠቡ፤ አሮንም ስጦታ አድርጎ በእግዚአብሔር ፊት አቀረባቸው፤ አሮንም ያነጻቸው ዘንድ አስተሰረየላቸው። |
በዚህም ውኃ በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ሁለመናውን ያጠራል፥ ንጹሕም ይሆናል፤ ነገር ግን በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ሁለመናውን ባያጠራ ንጹሕ አይሆንም።
ንጹሑም በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን በርኩሱ ላይ ይረጨዋል፤ በሰባተኛውም ቀን ያጠራዋል፤ እርሱም ልብሱን ያጥባል፥ ገላውንም በውኃ ይታጠባል፥ በማታም ጊዜ ንጹሕ ይሆናል።
ሙሴና አሮን የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ እንዲሁ በሌዋውያን ላይ አደረጉ፤ እግዚአብሔር ሙሴን ስለ ሌዋውያን እንዳዘዘው እንዲሁ የእስራኤል ልጆች አደረጉላቸው።
ከዚያም በኋላ ሌዋውያን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በአሮንና በልጆቹ ፊት አገልግሎታቸውን ይሠሩ ዘንድ ገቡ፤ እግዚአብሔር ሙሴን ስለ ሌዋውያን እንዳዘዘው እንዲሁ አደረጉላቸው።
ታነጻቸው ዘንድ እንዲህ ታደርግላቸዋለህ፤ ኃጢአትን የሚያነጻውን ውኃ እርጫቸው፥ በገላቸውም ሁሉ ምላጭ ያሳልፉ፥ ልብሳቸውንም ይጠቡ፥ ይታጠቡም።