ዘኍል 7:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለቀዓት ልጆች ግን መቅደሱን ማገልገል የእነርሱ ነውና፥ በትከሻቸውም ይሸከሙት ነበርና ምንም አልሰጣቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኀላፊነት የተሰጧቸውን ንዋያተ ቅድሳት በትከሻቸው መሸከም ስለ ነበረባቸው፣ ሙሴ ለቀዓታውያን ምንም አልሰጣቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለቀዓት ልጆች ግን በትከሻቸው በመሸከም ቅዱስ የሆኑትን ነገረሮች ማገልገል የእነርሱ ነበርና፥ ለእነርሱ ምንም አልሰጣቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእነርሱ ኀላፊነት የሚጠበቁት ንዋያተ ቅድሳት በትከሻቸው የሚሸከሙአቸው ስለ ሆኑ ሙሴ ለቀዓታውያን ሠረገሎችንም ሆነ በሬዎችን አልሰጣቸውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለቀዓት ልጆች ግን መቅደሱን ማገልገል የእነርሱ ነውና፥ በትከሻቸውም ይሸከሙት ነበርና ምንም አልሰጣቸውም። |
የእግዚአብሔርንም ታቦት በአዲስ ሰረገላ ላይ ጫኑ፥ በኮረብታውም ላይ ከነበረው ከአሚናዳብ ቤት አመጡት፥ የአሚናዳብ ልጆችም ዖዛ እና አሒዮ አዲሱን ሰረገላ ይነዱ ነበር።