ዘኍል 5:16 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም ያቀርባታል በእግዚአብሔርም ፊት ያቆማታል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ካህኑ ሴትዮዋን ያመጣትና በእግዚአብሔር ፊት እንድትቆም ያደርጋታል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ካህኑም ያቀርባታል በጌታም ፊት ያቆማታል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ካህኑ ሴትዮዋን ወስዶ በእግዚአብሔር ፊት እንድትቆም ያድርግ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ካህኑም ያቀርባታል፤ በእግዚአብሔርም ፊት ያቆማታል፤ |
መባውም የሚቃጠል መሥዋዕት ከላሞች መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርባል፤ በእግዚአብሔር ፊት እንዲሠምር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ፊት ያቀርበዋል።
የኢፍ መስፈሪያም አሥረኛ እጅ ገብስ ዱቄት ቍርባን ስለ እርስዋ ያምጣ፤ የቅንዓት ቍርባን ነውና፥ ኃጢአትንም የሚያሳስብ የመታሰቢያ ቍርባን ነውና ዘይት አያፍስስበት፥ ዕጣንም አይጨምርበት።