ኦርዮም ዳዊትን፦ ታቦቱና እስራኤል ይሁዳም በጎጆ ተቀምጠዋል፥ ጌታዬ ኢዮአብና የጌታዬም ባሪያዎች በሰፊ ሜዳ ሰፍረዋል እኔ ልበላና ልጠጣ ወይስ ከሚስቴ ጋር ልተኛ ወደ ቤቴ እሄዳላሁን? በሕይወትህና በሕያው ነፍስህ እምላለሁ! ይህን ነገር አላደርገውም አለው።
ዘኍል 32:6 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም ለጋድና ለሮቤል ልጆች አላቸው፦ ወንድሞቻችሁ ወደ ጦርነት ሲሄዱ እናንተ በዚህ ትቀመጣላችሁን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም የጋድንና የሮቤልን ነገዶች እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ እዚህ ተቀምጣችሁ ወገኖቻችሁ ወደ ጦርነት ይሂዱ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም ለጋድና ለሮቤል ልጆች እንዲህ አላቸው፦ “ወንድሞቻችሁ ወደ ጦርነት ሲሄዱ እናንተ በዚህ ትቀመጣላችሁን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ወገኖቻችሁ እስራኤላውያን ወደ ጦርነት ሲሄዱ እናንተ እዚህ መቅረት ትፈልጋላችሁን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም ለሮቤል ልጆችና ለጋድ ልጆች አላቸው፥ “ወንድሞቻችሁ ወደ ጦርነት ሲሄዱ እናንተ በዚህ ትቀመጣላችሁን? |
ኦርዮም ዳዊትን፦ ታቦቱና እስራኤል ይሁዳም በጎጆ ተቀምጠዋል፥ ጌታዬ ኢዮአብና የጌታዬም ባሪያዎች በሰፊ ሜዳ ሰፍረዋል እኔ ልበላና ልጠጣ ወይስ ከሚስቴ ጋር ልተኛ ወደ ቤቴ እሄዳላሁን? በሕይወትህና በሕያው ነፍስህ እምላለሁ! ይህን ነገር አላደርገውም አለው።