ዘኍል 32:2 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጋድና የሮቤል ልጆች መጥተው ሙሴንና ካሁኑን አልዓዛርን የማኅበሩንም አለቆች እንዲህ ብለው ተናገሩአቸው፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የሮቤልና የጋድ ሰዎች ወደ ሙሴ፣ ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛርና ወደ ማኅበረ ሰቡ መሪዎች መጥተው እንዲህ አሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጋድና የሮቤል ልጆች መጥተው ሙሴንና ካህኑን አልዓዛርን የማኅበሩንም አለቆች እንዲህ አሉአቸው፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ሙሴና አልዓዛር እንዲሁም ወደ ሌሎቹ የማኅበሩ መሪዎች ሄደው እንዲህ አሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆችም መጥተው ሙሴንና ካህኑን አልዓዛርን፥ የማኅበሩንም አለቆች እንዲህ ብለው ተናገሩአቸው፦ |
የሮቤልና የጋድ ልጆችም እጅግ ብዙ እንስሶች ነበሩአቸው፤ እነሆም፥ የኢያዜር ምድርና የገለዓድ ምድር ለእንስሶች የተመቸ ስፍራ እንደ ነበረ ባዩ ጊዜ፥
እግዚአብሔር በእስራኤል ማኅበር ፊት የመታው ምድር፥ አጣሮት፥ ዲቦን፥ ኢያዜር፥ ነምራ፥ ሐሴቦን፥ ኤልያሊ፥ ሴባማ፥ ናባው፥ ባያን፥ ለእንስሶች የተመቸ ምድር ነው፤ ለእኛም ለባሪያዎችህ እንስሶች አሉን።